ሰኞ ግንቦት 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ዛሬ በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1 ሺህ 40 ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው መመለስ ተችሏል።
ከእነዚህ ውስጥ 303 ሴቶች 90 ህጻናት እና 647 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል።
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው ከ23 ሺህ 640 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።
_
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n





