የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 85 ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸው ተገለፀ

0
1160

ሰኞ ግንቦት 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 85 ተሽከርካሪዎች በትናንትናው ዕለት መቀሌ መድረሳቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ፤ በትግራይ እና አፋር ክልሎች ለችግር ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሰራጨው የሰብዓዊ እርዳታ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል።

በዚህም በትናንትናው ዕለት የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 85 ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸውን ገልጿል።

በተመሳሳይ ወደ ሰሜኑ የአፋር ክልል አካባቢዎች በመጓዝ ላይ ያለና እስከ 36 ሺህ ለሚደርሱ ሰዎች የሚሆን ምግብ እና የሰብዓዊ እርዳታ በሚቀጥሉት ቀናት ይደርሳል ብሏል።

በተጨማሪም የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 130 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እያቀኑ መሆኑን የገለፀው የዓለም ምግብ ፕሮግራም፤ ይህም በተያዘነው የፈረንጆቹ ዓመት ወደ መቀሌ ከተጓጓዘው የሰብዓዊ እርዳታ በመጠን ትልቁ መሆኑ ገልጿል፡፡
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here