የዓለምአቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመተባበር በዝቋላ ወረዳ ለተፈናቀሉ ወገኖች የዕለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ አደረገ

0
766

ማክሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የዓለምአቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴም ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመተባበር በዝቋላ ወረዳ ከ6 ቀበሌዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ከአስር ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የዕለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ አድርጓል።

የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሽብርተኝነት በተፈረጀው የህወሃት ቡድን ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች አንዱ ነው። በቡድኑ ወረራ በርካታ ወገኖች ተፈናቅለዋል። በብሔረሰብ አሥተዳደሩ በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች የተለያዩ ድጋፎች እየተደረገላቸው ይገኛል።

ድጋፉን በቦታው ያስረከቡት በዓለምአቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የኢኮኖሚ ደህንነት አሥተባባሪ ሐስኒ ታራንጋ የተለያዩ ረጂ ድርጅቶችና መንግሥት ተፈናቃዮችን እያገዙ ቢሆንም እያገኙት ያለው ድጋፍ በቂ አይደለም ብለዋል።

ለ3 ሺህ 250 አባዎራዎች ወይም ከ19 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች ለአንድ ወር ፍጆታ የሚሆን ሙሉ ግብዓት ያካተተ የዕለት ደራሽ ምግብ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።

በቀጣይም ሌሎች ድጋፎች እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የዝቋላ ወረዳ አሥተዳዳሪ ታፈረ ሚሰነህ በበኩላቸው፤ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው በወረዳው ብቻ ከ18 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በጊዜያዊ የመጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በአካባቢው የፀጥታ ስጋት መኖሩ እና ተፈናቃዮች ያረፉበት አካባቢም ከፍተኛ ሙቀት ያለው በመሆኑ ያጋጠመው ችግር አሳሳቢ እንዳደረገውም አስረድተዋል።

መንግሥት በቡድኑ የተወረሩ አካባቢዎችን ነጻ አድርጎ የተፈናቀሉ ወገኖች ሕይወታቸውን እንዲመሩ ማስቻል እንደሚገባ ተናግረዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

_____
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here