አብዱረህማን ቃሲም የተባለው እና 528 ሺሕ የተለያዩ የውጪ አገር ገንዘቦችን በሕገ ወጥ መንገድ በቶጎ ጫሌ በኩል ወደ ወጪ አገር ይዞ ሊወጣ ሲል እጅ ከፍንጅ የተያው ግለሰብ ላይ ዐቃቢ ሕግ ከስ መሰረተ።
አብዱረህማን በተያዘበት ዕለት ሚያዝያ 26/2011 110 ሺሕ ድራም፣ 182 ሺሕ ዶላር እና 235 ሺሕ ሪያል ይዞ ከአገር ሊወጣ ሲል እጅ ከፍንጅ ድንበር ላይ መያዙ ታውቋል። ፖሊስ ለ20 ቀን በጊዜ ቀጠሮ ከቆየ በኋላ ዐቃቤ ሕግ ግንቦት 26/2011 በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አምስተኛ ወንጀል ችሎት ክስ መስርቷል።
ሲዘዋወር የተያዘው ገንዘብም በኤግዚቢትነት የተያዘ ሲሆን ተጠርጣሪው ጥፋተኛ ሆኖ ሲገኝ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል።
ክሱን የተቀበለው ፍርድ ቤቱ በዋስትና መብት ጥያቄ ላይ ክርክር ለማካሔድ ለሰኔ 19 ቀጠሮ ሰጥቷል።
ቅጽ 1 ቁጥር 32 ሰኔ 8 2011



