ብርሃንና ሰላም የኅትመት ዋጋ ጨመረ

0
579

ባለፈው ታኅሣሥ 2011 ከተደረገው የ16 በመቶ የኅትመት ዋጋ ጭማሪ በኋላ በየወሩ ከአምስት እስከ ዐሥር በመቶ ዋጋ ጭማሪ ሲያደርግ የነበረው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ከሚያዚያ ወር ጀምሮ በሥራ ላይ በነበረው ዋጋ ላይ የ6.2 በመቶ ጭማሪ አደረገ።

የኅትመት ጥራት፥ በጊዜ የማስተናገድ ችግርና ከፍተኛ የሀብት ብክነት እንዳለበት ዘወትር ቅሬታ የሚቀርብበት ማተሚያ ቤቱ፣ ባለፈው ዓመት 203 ሚሊዮን ብር ማትረፉ ይታወቃል። ማተሚያ ቤቱ 18 ጋዜጦችን የሚያትም ሲሆን በየጊዜው የሚደረገው የማተሚያ ዋጋ መጨመር በማንሰራራት ላይ ያለውን የኅትመት መገናኛ ብዙኀን ህልውና ፈታኝ እያደረገው መምጣቱን አሳታሚዎች ይናገራሉ።

ቅጽ 1 ቁጥር 32 ሰኔ 8 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here