የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሣሪያ ለማስመጣት ለሦስት ድርጅቶች ፈቃድ ተሰጠ

0
511

በቅርቡ በተለያዩ መኪኖች ላይ የሚገባው የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሣሪያ አስመጥቶ ለመግጠም የትራንስፖርት ባለሥልጣን ለሦስት አስመጪዎች ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ።

ፍቃዱን ካገኙት መካከልም ካሳ ሶፍትዌር ትራኪንግ ኃ.የተ.የግል ማኅበር አንዱ ሲሆን ሥራ አስኪያጁ ሰለሞን ካሳ እንዳሉት በአሁኑ ሰዓት ለናሙና ያህል 50 የፍጥነት መቆጣጠሪያ አስመጥተው የፍጥነት መገደቢያውን ለመግጠም የውጭ ምንዛሪው ከተፈቀደ በመጀመሪያ ዙር ከሁለት ሺሕ ያልበለጡ መሣሪያዎች እንደሚገቡ እና በቀጣይ ለሚገቡት ደግሞ በባለሥልጣኑ ፍላጎት ላይ ያተኮረ ይሆናል ብለዋል።

የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሣሪያ የሚገጠምላቸውም የንግድ መኪኖች፣ የጭነት ተሸከርካሪዎች እና የግል መኪኖች ሲሆኑ ባለሥልጣኑ ወደሚቆጣጠረው የመረጃ ቋት መረጃ የሚልክ መገኛ ጠቋሚ መሣሪያ (GPS) ይገጠምላቸዋል።

የመኪና ባለቤቶች የፍጥነት መቆጣጠሪያ መሣሪያን በመጠቀም እስከ 2 መቶ መኪኖችን መቆጣጠር እንደሚችሉ ታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 32 ሰኔ 8 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here