57 የምግብ ምርት ዓይነቶችን ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም ተከለከለ

0
731

የኢትዮጵያ ምግብ መድኀኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለሥልጣን 57 የተለያዩ ዓይነት የምግብ ምርቶችን ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀም አስጠነቀቀ። ባለሥልጣኑ የገበያ ጥናት ባደረበት ወቅት ምርቶቹ የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜያቸው በትክክል ያልተጻፈ፣ የተመረቱበት ጊዜ ያልተጠቀሰ፣ እንዲሁም አምራች ድርጅቶቻቸው ያልታወቁ መሆናቸውን ካረጋጋጠ በኋላ ነው ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ክልከላ የጣለባቸው።

ባለሥልጣኑ በሰባት የተለያዩ የምግብ ዘርፎች ከፋፍሎ 57 የምግብ ዓይነቶች ላይ ክልከላ የጣለ ሲሆን እነዚህም፤ በከረሜላዎች፣ በማር ምርቶች፣ የገበታ ጨው፣ የለውዝ ቅቤ፣ የኑግ ዘይት፣ አልሚ የሕፃናት ምግቦች እና አቼቶዎችን የንግድ ሥማቸውን በመጠቀም ከልክሏል። ከሰባቱ የምግብ ዘርፎች መካከልም በስፋት ገበያ ላይ የሚገኘውን “የስ ኮፊ” ከረሜላን ጨምሮ ሌሎች የኤሊፖፕ ምርቶችም የተከለከሉ ሲሆን በሕጻናት አልሚ ምግቦችም “ፋሚሊ ኀይል ሰጭና ገንቢ የሕጻናት ሽሮ፣ እና ሒሩት የሕጻናት አጃ” ጨምሮ ሌሎች የሕጻናት ምግቦች እንዲከለከሉ ሆነዋል።

ባለሥልጣኑም በጠቀሳቸው ምርቶች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግና ምርቶችም ኅብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው በአፋጣኝ እንዲሰበሰቡም አሳስቧል።

ቅጽ 1 ቁጥር 36 ሐምሌ 6 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here