ጠ/ሚ ዐቢይ በመዲናዋ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት እንጀምራለን ሲሉ ገለፁ

0
1065

ለዚህም የመደመር መንገድ መጽሐፍ ተሽጦ ካስገኘው ገንዘብ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን መመደባቸውን ገልፀዋል

ዕረቡ ሚያዚያ 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በአዲስ አበባ ውስጥ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት እንጀምራለን ብለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም የመደመር መንገድ መጽሐፍ ተሽጦ ካስገኘው ገንዘብ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ብር ድረስ መመደባቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኹሉም ዜጋ በእድሳት መርኃ-ግብሩ ላይ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሰርቪስ አሰጣጥ፣ በሥራ እድል ፈጠራ፣ በማዕድ ማጋራት እንዲሁም ኹሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ያማከለ ተመጣጣኝ የኑሮ እርከን መፍጠር እንዲቻል ከአመራሩ በቀጣይ የሚጠበቁ ኃላፊነቶችን ጠቁመዋል፡፡

ቤት ኪራይ ጭማሪ ላይ ቁጥጥር መደረግ እንዳለበት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ፕሮፐርቲ ታክስ ላይ ደሃውን ታሳቢ ያደረገ አሰራር መዘርጋት እንደሚጠበቅ ማሳሰባቸውን ዋልታ ዘግቧል፡፡

የመታወቂያ እደላን በተመለከተ ዲጂታል መታወቂያ እስኪወጣ ይቁም ሲሉም ገልጸዋል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here