የጀግኖች አርበኞችን ተጋድሎ የሚዘክር አውደርእይ ተከፈተ

0
1348

ዕረቡ ሚያዚያ 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመፃህፍት አግልግሎት የኢትዮጵያ የድል በዓል ቀንን ምክንያት በማድረግ በተቋሙ ካሉ የመዛግብት ስብስብ መሀል የጀግኖች አርበኞችን ተጋድሎ የሚዘክር አውደርእይ ከፍቷል።

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝደንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ አውደርእዩን በከፈቱበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ጀግኖች አርበኞች ደማቸውን አፍስሰው ያቆይዋትን ኢትዮጵያ እንዳትጠፋ ኹሉም ሰው ዘብ ሊቆም እንደሚገባው ጠቁመው፤ አገርን ለመንግስት ብቻ መተው አይገባም ብለዋል። ኢትዮጵያን በሚመለከት ጉዳይ ላይ ኹሉም ዜጎች የአገሪቷ መንግሥት ናቸው።

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመፃህፍት አግልግሎት ዋና ዳይሬክተር ይኩኖ አምላክ መዝገቡ በበኩላቸው፤ ተቋሙ ጀግኖች አርበኞችን የሚዘክር ሥራ በመስራቱ ትልቅ ኩራት ይሰማዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመፃህፍት አግልግሎት የከፈተው አውደ ርእይ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 28 ድረስ ይቀጥላል መባሉንም ኢፕድ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ የድል በዓል ላይ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ተገኝተው የአበባ ጉንጉን ያሰቀምጣሉ። እንዲሁም 47 የውጭ እንግዶች በተገኙበት እንደሚከበር በመድረኩ ተመላክቷል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here