ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ሥምምነት ተፈራረሙ

0
1206

ማክሰኞ ግንቦት 2 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ዝርዝር ተግባራት ላይ ሥምምነት መፈራረማቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሥምምነቱ ኹለቱ አገራት በባዮ ቴክኖሎጂ፣ በህዋ ሳይንስ እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው ነው ተብሏል፡፡

እስከ 2025 በሚቆየው ይህ የትብብር ሥምምነት የሰው ሃይል ስልጠና፣ የባለሙያ ልውውጥ፣ በኢኖቬሽን ሰታርትአፕ እና በሌሎች የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል፡፡

መሰከረም ወር ላይ የተቋቋመው የኹለቱ አገራት የቴክኒክ ኮሚቴ ያዘጋጀውን የትብብሩን ዝርዝር ተግባራት ሥምምነት በኢትየጵያ በኩል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ፒ ኤች ዲ) እና በደቡብ አፍሪካ በኩል ድግሞ የሳይንስና ኢኖቬሽን ዲፓርትመንት ተወካይ ሚስተር ዳን ዱ ቶይት ፈርመውታል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ፣ በምርምር እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ደቡብ አፍሪካ ያላትን የተሻለ ልምድ ኢትዮጵያ ትወስዳለች ብለዋል፡፡

ኹለቱ አገራት በሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ሥምምነት ከዚህ በፊት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡
___
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here