መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናየትራንስፖርት አገልግሎቱን በሚያስተጓጉሉ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ

የትራንስፖርት አገልግሎቱን በሚያስተጓጉሉ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ

ማክሰኞ ግንቦት 2 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ጋር ተያይዞ አገልግሎቱን በተገቢው መንገድ በማይሰጡ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ወይም የትራንስፖርት አገልግሎት በሚያቋርጡ ተሽከርካዎችና አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር እጸገነት አበበ እንደገለጹት ማንኛውም የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት ድጋፍ ሰጪዎችን ጨምሮ በተመደቡበት የስምሪት መስመር በመገኘት በተቀመጠው የታሪፍ መጠን ብቻ አገልግሎቱን መስጠት ይገባቸዋል፡፡

በጥናት መመለስ የሚገባቸው ጉዳዮች ካሉም ቢሮው አሰራሩን በመፈተሽ በሂደት ምላሽ እሰጣለሁ ብሏል፡፡

በሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት በኪራይ ውል አገልግሎት የሚሰጡ ድጋፍ ሰጪዎች ከቢሮው ጋር በገቡት ውል መሠረት የትራንስፖርት አገልግሎት የማይሰጡትን ቢሮው ከስምምነት ውል ውጪ እንደሚያደርጋቸው አውቀው ወደ ነበሩበት መስመር በፍጥነት እንዲገቡና ሥራቸውን እንዲሰሩም ከቢሮው ጥሪ ተላልፏል፡፡

ከነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ ኅብረተሰቡን ከታሪፍ በላይ በሚያስከፍሉ፣ መስመር በሚያቆራርጡ፣ የመስመር ታፔላ በማይሰቅሉ (ከእይታ ውጪ በሚያደርጉ)፣ ታሪፍ በማይሰቅሉ (በማይለጥፉ)፣ ተሽከርካሪዎችን ከተፈቀደላቸው አገልግሎት ውጪ የሚያውሉ የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ አሽከርካሪዎች ካሉ ከወዲሁ ጥብቅ ጥንቃቄ በማድረግ ሥራቸውን በተገቢው መንገድ እንዲያከናውኑ ጠይቋል፡፡

ቢሮው ህግና መመሪያዎችን ተከትለው በማይሰሩ የሕዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ህብረተሰቡ ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዳይዳረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚሰራም የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች