595 ሺህ ኩንታል ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ መድረሱ ተገለፀ

0
1601

ዕረቡ ግንቦት 3 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን 595 ሺህ ኩንታል NPSB የአፈር ማዳበሪያ “MV JOSCO GUIZHOU” በተባለች መርከብ ዛሬ ንጋት ላይ ጅቡቲ ወደብ መድረሱን አስታውቋል።

ኮርፖሬሽኑ ለ2014/15 የሰብል ዘመን ከሞሮኮው የአፈር ማዳበሪያ አምራች ኩባንያ ከገዛው 7 ሚሊዮን 875 ሺህ 523 ነጥብ 4 ኩንታል NPS ፋሚሊ (የናይትሮጅን፣ ፎስፌት እና ሰልፈር ውህድ) ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ 7 ሚሊዮን 299 ሺህ 150 ነጥብ 5 ኩንታል (92 ነጥብ 7 በመቶ) ጅቡቲ ወደብ ደርሶ ወደ አገር ውስጥ እየተጓጓዘ መሆኑንም አስታዉቋል።

ቀሪው 576 ሺህ 372 ነጥብ 9 ኩንታል NPS እና NPSB ማዳበሪያ ግንቦት 9 ቀን 2014 ጅቡቲ ወደብ እንደሚደርስ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል በቅርቡ በኹለት ዙር ጅቡቲ ወደብ የደረሰው 1 ሚሊዮን ኩንታል ዩሪያ ለአርሶ አደሩ እየቀረበ ይገኛል። በቅርብ ቀናትም ተጨማሪ ዩሪያ ማዳበሪያ ወደብ እንደሚደርስ ኮርፖሬሽኑ አስታዉቋል።

በአጠቃላይ ከጥር ወር አንስቶ እስከ ዛሬ ግንቦት ዛሬ 3 ቀን 2014 ድረስ 8 ሚሊዮን 299 ሺህ 150 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ ደርሷል።

ከዚህ መጠን ውስጥ እስከ አሁን 6 ሚሊዮን 292 ሺህ 229 ኩንታል (76 በመቶ) የአፈር ማዳበሪያ በክልል ዩኒየኖች አማካኝነት ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ እንደሚገኝም ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነዉ መረጃ አመላክቷል።
___
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here