በሚያዝያ ወር ብቻ 33 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡ ተገለፀ

0
884

ሐሙስ ግንቦት 4 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በሚያዝያ ወር ብቻ 33 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት፤ በሚያዝያ ወር ከ35 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ 33 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል ብለዋል፡፡

ገቢው የተገኘው ከአገር ውስጥ ታክስ፣ ከዉጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ ሲሆን፤ አፈፃፀሙ ካለፈው በጀት አመት ወር ጋር ሲነፃፀር የ31 ነጥብ 19 በመቶ ዕድገት እንዳለው ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ ውጤቱ መመዝገብ የቻለው የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች በትብብርና በትጋት በመስራታቸው መሆኑን ጠቅሰው፤ በተገኘው ስኬት ለተሳተፉ አጋር አካላትና ግብር ከፋዮች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
_______________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here