ሐሙስ ግንቦት 4 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2014 የሐጅ ተጓዦች ምዝገባ መጀመሩን በመግለፅ፤ ተጓዦች ሊያሟሉ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት የሐጅ ተጓዦች ሊያሟሉ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፦
1. ለሐጅ የሚሄደው ግለሰብ ከ65 ዓመት በታች የሆነ
2. የኮቪድ 19 ክትባት የወሰደ እና የማረጋገጫ ወረቀቱን የያዘ
3. የታደሰ ፓስፖርት ያለው፤ ፓስፓርት የሌለውና ጊዜው ያለቀ ከሆነ ወደ ጦር ሃይሎች ሆላንድ ኢምባሲ አጠገብ ዋናው ቢሮ በመምጣት ሂደቱን ማፋጠን ይችላል።
4. ባልና ሚስት አብረው የሚሄዱ ከሆነ የጋብቻ ማረጋገጫ ያስፈልጋል። ግዴታ ነው!
5. ልክ የዛሬ ወር በረራ ስለሚጀመር ቶሎ በመመዝገዝ ሂደቱን የተቀላጠፈ ማድረግ እንደሚቻል የተገለፀ ሲሆን፤
በተጨማሪም የሐጅ ተጓዦች አጠቃላይ አገልግሎት ዋጋ 83 ሺህ 500 ብር መሆኑንም ምክር ቤቱ ያወጣው የዋጋ ዝርዝር አመላክቷል።
የዋጋ ዝርዝሩን እና ብር የሚገባባቸው ባንክ እና ቁጥሮቻቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን ሀጃጁ ባንክ ያስገባበትን ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ አድርጎ በመያዝ ኦርጅናሉን ይዞ መምጣት እንደሚጠበቅበትም ምክር ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳስቧል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n



