አማራን ሕዝብ ደህንነት ለማስጠበቅ ያለመ የተደራጀ ሥልጠና ሊሰጥ መሆኑ ተገለፀ

0
1428

በክልሉ ለተከታታይ 4 ቀናት የጦር መሳሪያ ምዝገባ ይካሄዳል ተብሏል

ሰኞ ግንቦት 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) አማራን ሕዝብ ደህንነት ለማስጠበቅ ያለመ የተደራጀ ሥልጠና ሊሰጥ እንደሆነና፤ ከግንቦት 9 ቀን 2014 ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት የጦር መሳሪያ ምዝገባ እንደሚካሔድ የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።

ከዚህ በፊት ያልተመዘገበ ማንኛውም የጦር መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በአካባቢው በሚገኙ የምዝገባ ማዕከላት በመገኘት እንዲያስመዘግብ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አሳስቧል።

የቢሮው ሀላፊ ደሳለኝ ጣሰው ለአሚኮ እንዳስታወቁት የጦር መሳሪያ ምዝገባው የአማራን ሕዝብ ደኅንነት ለማስጠበቅ አጋዥ ሀይል ለማጠናከር ያለመ ነው።

የትግራይ ወራሪ ቡድንን የጥፋት መንገድ ተጋሪዎች የአማራን ሕዝብ አንድነት ለመሸርሸር በብሔርና በሃይማኖት ሽፋን የተለያዩ አጀንዳዎችን እየዘረጉ መሆኑን ያነሱት ቢሮ ሀላፊው፤ የሽብር ቡድኑ አሁንም ወደ ዳግም ጦርነት ለመግባት ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ በተጨባጭ እያሳየ ነው ብለዋል።

የጥፋት ሀይሉን ዓላማ ለማክሸፍ ከመንግሥት የጸጥታ ኀይል በተጨማሪ ማንኛውም የጦር መሳሪያ ያለው ምዝገባ ካካሔደ በኋላ የተደራጀ ሥልጠና እንዲወስድም ይደረጋል ብለዋል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here