የዘንድሮ የአባቶች ቀን “ክብርና ምስጋና ትውልድን በማተካካት አገራችንን ለሰሯት አባቶች” በሚል መሪ ቃል ከግንቦት 15 እስከ 19 ይከበራል

0
1451

 

ሰኞ ግንቦት 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ዘንድሮ የሚከበረው የአባቶች ቀን “ክብርና ምስጋና ትውልድን በማተካካት አገራችንን ለሰሯት አባቶች” በሚል መሪ ቃል ከግንቦት 15 እስከ ግንቦት 19 ቀን 2014 ድረስ እንደሚከበር የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታዉቋል።

በዓሉ ለ5 ተከታታይ ቀናት በመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ከሚረዱ አባቶች፣ ከወጣቱ ትውልድ እና ከተለያዩ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር በመሆን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ተብሏል።

ለአንድ አባት አንድ ምሳ ማብላት እንዲቻል ለበዓሉ የተዘጋጁትን ፖስት- ካርዶች አንዱን በ100 ብር በመግዛት ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ መቅረቡን ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

የበዓሉ አንዱ አካል በሆነው 1 ሺህ አባቶችን ጋቢ የማልበስ መርሐ- ግብር ላይ ከአንድ ሰው ጀምሮ ኹሉም የማህበረሰብ ክፍል የተቻለውን ያህል ጋቢ በማምጣት በይፋ አባቶችን ጋቢ እንዲያለብስም ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here