ከአዲስ አበባ ሐረር የሚዘልቀው መንገድ ምዕራብ ሐረርጌ ላይ ተዘግቷል

0
1299

ትናንት ሰኞ መስከረም 5/2012 ምሽት አራት ሰዓት ላይ ከሐረር ወደ አዲስ አበባ ሲያቀና የነበረ ከባድ መኪና ምዕራብ ሐረርጌ ቆቦ አካባቢ በሰርግ ስነ ስርዓት ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ አደጋ በማድረሱ መንገዱ ዝግ ሆኖ እንዲያድርና እንዲውል እንደተደረገ የአዲስ ማለዳ ምንጮች ከስፍራው አረጋግጠዋል።

ምንጮች እንደተናገሩት እንደተናገሩት በአካባቢ የሕግ አካላት ባለመምጣታቸው መንገዱ ምፍትሔ ሊበጅለት እንዳልቻለና ከ1 ሽሕ በላይ መኪኖች በመንገዱ ዳር ላይ ቆመው የመንገዱን መከፈት እየተጠባበቁ እንደሆነም ጠቁመዋል። መንገዱ አደጋው ከደረሰበት እስከ ሰባት ኪሎ ሜትር ድረስ ዝግ እንደሆነም አዲስ ማለዳ ከስፍራው ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

ከባድ መኪናው ባደረሰው አደጋ እስካሁን የሟቾች ቁጥር በውል እንደማይታወቅ የተገለጸ ሲሆን በአካባቢ የአዲስ ማለዳ ምንጮች ግን ዐስር ያህል ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ተናግረዋል። አሽከርካሪው በአካባቢው ሕብረተሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here