በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ቀጣይ ውይይት በሱዳን ይካሔዳል

0
867

በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሰሞኑን በግብፅ ካይሮ ሲመክሩ የነበሩት ሦስቱ የናይል ተፋሰስ አገራት ቀጣይ ውይይታቸውን በሱዳን ካርቱም እንዲሆን ወስነዋል። የሦስትዮሽ ውይይቱ የቴክኒክ ጉዳዮችን ያልተነሱበት እንደነበርና ኢትዮጵያ በግብፅና በሱዳን በቀረቡ ሀሳቦች ላይ ለመወያየት ፈቃደኛ ባለመሆኗ እንደሆነ ምንጮች አስታውቀዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞም አስቸኳይ የሦስትዮሽ ስብሰባው በሱዳን እንዲካሔድ እንዲወሰን ምክንያት ሆኗል።

በቀጣይ በሚካሔደው የሱዳኑ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ በሚገባ እንድትሳተፍና በቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ተደርሶ በ2007 በሱዳን ካርቱም የተገባው ስምምነት እንድታከብር ጥሪ ቀርቧል።

በተያዘው ወር መጨረሻ ቀናት በሱዳን ካርቱም ይካሔዳል ተብሎ የሚጠበቀው የሦስቱ አገራት ውይይት በርካታ አዳዲስ ውሳኔዎችና በግድቡ የቴክኒክ ጉዳይ ላይም ሰፋ ያሉ ውይይቶች ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ጥናት የሚያደርጉት ገለልተኛ የሳይንቲስቶች ቡድንም በቀጣይ የሦስቱ አገራት የውሃ እና መስኖ ሚንስትሮች ጉባኤ እንደሚኖርም አስታውቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here