መዝገብ

Author: ኤርሚያስ ሙሉጌታ

ዩኤስ ኤይድ እና አዋሽ ባንክ የ6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረሙ

የአሜሪካው ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤይድ እና አዋሽ ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን አነስተኛ ገንዘብ ተቋማት፣ እነዲሁም አነስተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የግብርና እንቅስቃሴዎችን በገንዘብ ለመደገፍ የ6ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ጋራ ስምምነት ተፈራረሙ። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ግብርና አሰራር ለማዘመን እንዲሁም አርሶ አደሮች…

በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ በተደረገው ድርድር አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ መካከል በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ታላቁን የኅዳሴ ግድብ በሚመለከት ሲደረግ በቆየው ድርድር አመርቂ ተጨባጭ  ውጤቶች መመዝገባቸውን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በትዊተር ገጻቸው አስታወቁ። በአራት ዙር ሲደረግ የነበረው የሦስቱ አገራት ድርድር ያለ ፍሬ መቋጨቱን ተከትሎ አሜሪካ…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ጥር 6/2012

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አስተዳደር የሚያደርስባቸው የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ሠራተኞች ተናገሩ::  ይሁን እንጂ አየር መንገዱ በበኩሉ ተቋሙ በጥብቅ ሥነ-ምግባር በመመራቱ የተቋሙን ገጽታ ለማጠልሸት ጥረት የሚያደርጉ ሠራተኞች ወቀሳ ነው ሲል ክሱን አስተባብሏል። (ኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ)…

የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ የልደት በዓል በጎንደር እየተከበረ እንደሚገኝ ተገለጸ

የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ 201ኛ የልደት በዓል በጎንደር ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ እንደሚገኝ የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘገበ ። ”ጥምቀትን በጎንደር” የማክበር የባህል ሳምንት አካል ሆነው የአጼ ቴዎድሮስ ልደት ክብረ በኣል ከዛሬ ጥር 6/2012 ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩ እንደሚቀጥል ታውቋል። የጎንደር…

በዘንድሮ 2012 የመራጮች ምዝገባ ጊዜ ከመጋቢት 29-ሚያዝያ 28 እንደሚሆን ተገለጸ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የ2012 አገራዊ የምርጫ መርሃ ግብርን ይፋ ባደረገበት ወቅት የመራጮች የምዝገባ ቀናት ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 28/2012 ለአንድ ወር የሚቆይ እንደሚሆን አስታወቀ። በአገራዊ መርጫ መርሃ ግብሩ ላይ እንደተገለፀው ከመራጮች ምዝገባም በተጨማሪ ለመራጮች ትምህርትና መረጃ የመስጫ ጊዜ የታወቀ ሲሆን…

የካናዳ ኢምባሲ በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርትን ለማጎልበት በጋራ ለመስራት መስማማቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ የሚገኘው የካናዳ ኢምባሲ በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምሀርት ተቋማትን ለማጠናከርና ድጋፍ ለማድረግ ከኢፌዲሪ ሳይነስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለማስራት ስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቀ። ኢምባሲው በቴክኒክና ሙያ፣ በሳይነስና በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግና ለማጠናከር የተስማማ ሲሆን ሴቶችን በማብቃት እንዲሁም በሌሎች…

በቀጣይ ስድስት ወራት አዲስ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ግንባታ እንደሚጀመር ተገለጸ

በተያዘው በጀት ዓመት ኹለተኛው አጋማሽ ላይ በትልቅነቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ የሆነ አየር ማረፊያ ለማስገንባት ዝግጅት መጠናቀቁቀን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ። አየር መንገዱ በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ እና በዝቋላ መካከል በሚገኝ አካባቢ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለማስገንባት ዕቅድ ይዞ ቦታ መረጣውም…

ኹለት የትግራይ ቴሌቪዥን የአማረኛ ክፍል ባልደረቦች በአሶሳ መታሰራቸውን ትግራይ ቴሌቪዥን አስታወቀ

አዲስ አበባ የሚገኘው የትግራይ ቴሌቪዥን የአማረኛው ክፍል ባልደረቦች ለስራ በሔዱበት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ መታሰራቸውን ትግራይ ቴሌቪዥን የአማረኛ ዝግጅት ክፍል ለአዲስ ማለዳ ተናገረ። ዝግጅት ክፍሉ ተወካይ አስተባባሪ ቴዎድሮስ አለማየሁ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት በአሶሳ ከተማ በሚካሔደው እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የውይይት…

”በእምነት ላይ የነገሠው የ‹ነብይነት› ለምድ

ሰዎች ትክክለኛውን መንገድ ያሳዩናል፣ ቅዱሱን የእግዚአብሔር ቃል ያስተምሩናል፣ በትክክለኛውም መንገድ ይመሩናል ባሏቸው እና ራሳቸውን ‹‹ነብያት›› ብለው በሚጠሩ ግለሰቦች ግፍ ሲፈጸምባቸው እና እንባቸውም በአደባባይ ሲፈስ መታዘብ ከጀመርን ዋል አደር ብለናል። በዚህም ረገድ በእነዚህ ራሳቸውን ከፈጣሪ የተላኩ ‹‹መልዕክተኞች›› ወይም ‹‹ነብያቶች›› ብለው በሚጠሩ…

በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ

ጥር 1/2012// በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 30/2012 ምሽት ላይ በኹለት ተማሪዎች መካከል በተከሰተ ፀብ የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን የዩኒቨርስቲው ፕሬዘዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አየለ አዳቶ ለዶቼ ቬለ ተናገሩ። በተጠቀሰው ቀን በተፈጠረው ፀብ ህይወቱ ያለፈው የአንደኛ ዓመት ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ አስከሬን ለምርመራ…

የትግራይ ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር የሕግ አማካሪ ዘርአይ ወልደሰንበት ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸው ተገለጸ

ከ1/09/2011 ጀምሮ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የትግራይ ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር የሕግ አማካሪ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩት ዘርኣይ ወልደሰንበት ‹‹መገፋት እና በደል እየደረሰብኝ›› ነው በሚል ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን አስታወቁ። ዘርኣይ ለትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዘዳንት ባስገቡት መልቀቂያ ደብዳቤ ላይ በክልሉ ተመድበው በሚሰሩበት የኃላፊነት…

ሔኒከን ቢራ ፋብሪካ የሰራተኛ ቅነሳ ሊያደርግ ነው መባሉን አስተባበለ

ሔኒከን ቢራ ፋብሪካ በቅርቡ ሰራተኛ ቅነሳ ሊያደርግ ነው ተብሎ የሚናፈሰው መረጃ ሐሰት እና ከእውት የራቀ እንደሆነ አስታወቀ። የሔኒከን ቢራ ፋብሪካ ሕዝብ ግንኙነትና ማርኬቲንግ ኃላፊ ፍቃዱ በሻህ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት በፋብሪካው ዘንድ ምንም አይነት ሰራተኛ የመቀነስም ሆነ የማባረር ፍላጎትም ሆነ አዝማሚያ…

በቀን እስከ 400 ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ተገለጸ

ወደ ኢትዮጵያ በአማካይ ከ300 እስከ 400 የሚሆኑ ኤርትራውያን ስደተኞች ድንበር አቋርጠው እንደሚገቡ በትግራይ ክልል የሚገኘው የእንዳባ ጉና ስደተኛ ጣቢያ አስታወቀ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጣቢያውን አስተባባሪ ሐዱሽ ኪዳኔ በመጥቀስ ባወጣው ዘገባ ላይ፣ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ…

ከሸገር እስከ የፍቅር ሐይቅ

አዲስ ማለዳ ጎዞዋን ቀጥላለች። ኅዳር 25/2012 ከረፋዱ 4 ሰዓት በመስቀል አደባባይ እንድንገኝ የተያዘው ቀጠሮ ላይ ሰዓት ማርፈድ በጋዜጠኞች መባሱ በሰዓቱ ለደረስነው አስደንጋጭ ነበር። ‹ጉዞው ተሰረዘ እንዴ?› በሚያስብል አኳኋን ከአንድ እጅ ጣቶች የማንበልጥ ተጓዥ ጋዜጠኞች ነበርን በስፍራው የተገኘነው። ደቂቃዎች ነጉደው መጀመር…

ከ7.7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃና ዶላር መያዙ ታወቀ

በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኅዳር 30/2012  ምሽት 3 ሰዓት ከብር 7ነጥብ 7 ሚሊዬን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ የገቢዎች ሚንስቴር እንዳስታወቀው  በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኢት 45074/14652 ኮንቴነር የጫነ ተሽከርካሪ ሀሰተኛ ሰነድ በመያዝ…

በወለጋ ዩኒቨርስቲ በሦስት ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለፀ

በወለጋ ዩኒቨርስቲ ትናንት ኅዳር 30/2012 እና ዛሬ ማለዳ ታኅሳስ 1/2012 በሦስት ዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው በትናንትናው ዕለት በወለጋ ዩኒቨርስቲ በኹለት ተማሪዎች ላይ ጉዳት ደረሰ ሲሆን ዛሬ ማለዳ ላይም በአንድ ተማሪ ላይ ጉዳ…

ዳሰሳ ዘማለዳ ኅዳር 30/2012

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በኖርዌይ ኦስሎ በተዘጋጀ ደማቅ ዝግጅት የኖቤል ሽማታቸውን ተቀብለዋል። በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ በርካታ ታዋቂ ግለሰቦችና ቀድሞ የኖቤል ሽልማት አሸናፊዎች ተገኝተዋል።(አዲስ ማለዳ) …………………………………………………………………………….. የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ በሚል በአማርኛ የሚታወቀው እና  በትግርኛ ምህፃሩ ዴምህት ራሱን አክስሞ ከህወሓት…

የተለያዩ የ19 አገራት ገንዘቦች በሕገ ወጥ መንገድ በአንድ ግለሰብ አማካኝነት ከአገር ሊወጣ ሲል ተያዘ

ከድሬዳዋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ወደ ጅቡቲ የሚያቀና መንገደኛ የ19 የተለያዩ አገራት መገበያያገንዘቦችን ይዞ ሊወጣ ሲል በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጣቢያ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውሏል። አሕመድ ኡስማን የተባሉ ግለሰብ በድሬዳዋ አየር ማረፊያ በተደረገባቸው ፍተሻ የተለያዩ አገራትን ገንዘቦች ለማስወጣት እየሞከሩ እንደነበር ተደርሶባቸዋል።…

የኢትዮጵያ ፣ሱዳንና ግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባ ተጠናቀቀ

በአሜሪካ ዋሽንግተን ሲካሔድ የቆየው የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባ ተጠናቋል። በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ ሲመክር የቆየው የሦስቱ አገራት የሚንስትሮች ስብሰባ በውሃ ሚንስትሮች ደረጃ የተካሔዱትን የባለሙያዎች ስብሰባ ያመጡትን ለውጦች ተመልክቷል። በቀጣይ የሚካሄዱ መሰል ኹለት ስብሰባዎችም በግደቡ የውሃ አሞላል እና አስተዳደር…

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ አጣሪ የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃን በተመለከተ ተቃውሞ እንዳላቸው ገለፁ

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የነፃ ሐሳብና በነፃነት ሀሳብን መግለጽ ጥበቃና አበረታች ልዩ መርማሪ ዴቪድ ካየ በቅርቡ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ለውይይት ቀረበውን የጥላቻ ንግግርና የሐሰት መረጃን በተመለከተ ተቃውሞ እንዳላቸው አስታወቁ። ዛሬ ኅዳር 29/2012 በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ  መግለጫ የሰጡት…

14ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው

14ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበ ይገኛል። “ህገ-መንግስታዊ ቃልኪዳናችን ለዘላቂ ሰላም”! በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ እየተከበረ የሚገኘው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ኹሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች በአንድነት የሚገናኙበት ቦታ እንደሆነም በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙ የመንግስት…

በጎንደር ዩኒቨርስቲ የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉ ተገለፀ

በጎንደር ዩኒቨርስቲ ትናንት ኅዳር 28/2012 አንድ የኹለተኛ ዓመት ተማሪ ህይወት ማለፉን የጎንደር ዩኒቨርስቲ አስታውቋል። ትናንት ንጋት ላይ በዩኒቨርስተው የቬተርናሪ ፋርማሲ የኹለተኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ማሾ ዑመር በደረሰበት ጉዳት ሕክምና ሲደረግለት የቆየ ቢሆንም አመሻሽ ላይ ህይወቱ ማለፉን ዩኒቨርስቲው ባውጣው የሀዘን መግለጫ…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 29/2012

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለኅብረተሰቡ ያቀረበውን የድጎማ ማሻሻያ 5 ቢሊዮን ብር እንደማይከፍል አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። (ፋና ብሮድካስቲንግ) ………………………………………………………… በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ የትምህረት ተቋማት በፌደራል ፖሊስ እንዲጠበቁ መወሰኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 26/2012

1-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የ2019 የኖቤል የሰለም ሽልማትን በመጪው ማክሰኞ ኅዳር 30/2012 ኖርዌይ ኦስሎ በመገኘት ይቀበላሉ።በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የኖቤል ኮሚቴው የሰላም ሽልማቱ ይበረከታል ተብሎ ይጠበቃል።ጠቅላይ ሚኒስትር በኖርዌይ ቆይታቸው ከአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልቤርግ እና…

በህገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ሊወጣ የነበረ አኩሪ አተርና ማሾ ምርት መያዙ ተገለፀ

ከገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በተካሄደው ህገ-ወጥ ንግድ ክትትልና ቁጥጥር ሥራ ወደ ኬኒያ ሊወጣ ሲል አኩሪ 1350 ኩንታል አኩሪ አተር እና 1295 የማሾ ምርት በቁጥጥር ስር ዋለ። በድምሩ 2,645 ኩንታል ምርት ኢትዮጵያ ምርት ገበያ ለሽያጭ…

እናት ባንክ ከ2መቶ ሚሊዮን ብር በላይ አተረፈ

እናት ባንክ በ2011 በጀት ዓመት 201 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ። ባንኩ በተጠቀሰው ዓመት ከታክስ በፊት 231 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገብ እንደቻለም ለማወቅ ተችሏል። እናት ባንክ በዓመታዊ ሪፖርቱ ላይ እንዳስታወቀው በ2011 በጀት ዓመት ከቀዳሚው ዓመት…

ደኢሕዴን ‹‹የፓርቲውን ውሕደት አስፈላጊነት እና ቀጣይ ትግል አቅጣጫዎች ››በሚል ርዕስ በሐዋሳ ውይይት ጀመረ

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የፓርቲ ውሕደት አስፈላጊነት እና የቀጣይ ትግል አቅጣጫዎች በሚል ርዕስ በሐዋሳ ዉይይት እያካሄደ ይገኛል። በውይይቱ ላይ የፓርቲ ውሕደት መነሻዎች እና የፓርቲ ውሕደት አስፈላጊነት፣ የፓርቲ ውሕደት ጥናት ሂደት እና አፈጻጸም ፣ የውሕደት አጃንዳ ውሳኔ እና የውሕድ ፓርቲ…

ኢትዮጵያ ሳተላይት የምታመጥቅበት ቀን በሦስት ቀናት ተራዘመ

ኢትዮጵያ በታሪክ የመጀመሪያዋ የሆነችውን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ወደ ሕዋ ለመላክ በታኅሳስ 7/2012 መርሃ ግብር ተይዞለት የነበረ ቢሆንም በሦስት ቀናት እንዲገፋ መደረጉ ታወቀ። ሳተላይቷ ከቻይና የምርምር ጣቢያ ወደ ሕዋ የምትመጥቅ ሲሆን፤ በከተማው ያለው የአየር ሁኔታ ሳተላይቷን ወደ ሕዋ ለማስወንጨፍ አስቸጋሪ በመሆኑ…

ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 23/2012

1-በሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ና የፀጥታ ኃይሎች ግድያ የተጠረጠሩ 55 ግለሰቦች ላይ ዛሬ ኅዳር 23/2012 የክስ ማመልከቻ መደመጥ ጀምሯል። በነሻምበል መማር ጌትነት መዝገብ ተጠርጥረው በማረሚያ ቤት ከሚገኙት መካከል 14 ተጠርጣሪዎች በማደራጀት፣ በመምራት የክልሉን ከፍተኛ ባለስልጣናትና የፖሊስ አባላትን በመግደልና…

በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ ሲካሔድ የቆየው ስብሰባ ተጠናቀቀ

በኅዳር 5 እና 6/2012 በአዲስ አበባ በኅዳሴው ግድብ የውሃ ሙሊት እና ውሃ አለቃቀቅ ዙሪያ ምክክር ተደርጎ ዕልባት ላይ ባልተደረሰባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ ሲወያዩ የቆዩት የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የውሃ ሚንስትሮች ስብሰባ ዛሬ ኅዳር 23/2012 ተጠናቋል። የኢፌዴሪ ውሃ፣ መስኖ…

This site is protected by wp-copyrightpro.com