ኢትዮጵያ በዓመት ከሦስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ የምታስገባው የነዳጅ ምርት ከአቅርቦት ሰንሰለት ችግር ጋር በተያያዘ ለብክነት እየተዳረገ እንደሆነ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ኮዋንግ ቱትላም (ዶ/ር) ዋቢ አድርጎ ኢዜአ ዘግቧል።
የነዳጅ ምርቶች ወደ አገር ውስጥ በሚገቡበት ወቅት በሕገ ወጥ ንግድ ምክንያት ብክነት እያጋጠመ እንደሆነና ይህም ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መንስኤ እስከ መሆን መድረሱ ተገልጿል። ይህንም ችግር ለመግታት የነዳጅ ተቋማት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንደሚኖርባቸው የተጠቆመ ሲሆን፥ ለነዳጅ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ እንዲኖራቸው ማድረግ እንደሚያስፈልግ ሚንስትር ዲኤታው አስታውቀዋል። ኮዋንግ አያይዘውም የነዳጅ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ በክልሎች መሰጠቱ በምርቶች አቅርቦት ሒደት ላይ ከብክነት ፀድቶ ለተጠቃሚው ለማድረስ ያለመቻሉን ተናግረዋል።



