ዳሰሳ ዘ ማለዳ ረቡዕ መስከረም 14/2012

0
739
  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢዜማ ፓርቲ መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከኢሳት የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ወቅት ምርጫ ቦርድን እንደ አዲስ ለማቋቋም ወጣውን አዋጅ በተመለከተ የተዛባ መረጃ ተናግረዋል በሚል ማስተካከያ እንዲያወጡ በደብዳቤ አሳስቧል።(አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………

  • በባለፈው ዓመት 2011 በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች በተፈጠሩት ግችቶች 1 ሽሕ 229 ሰዎች ህይወት መጥፋቱ የታወቀ ሲሆን ፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞም 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ገደማ የሚገመት ንብረትም መውደሙን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል። በሰዎች ህይወት መጥፋ እና ንብረት መውደም ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ 1 ሽሕ 323 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ክስ ተመስርቶባቸዋል። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………………

  • በአገር ውስጥ ከሚገኙ በርካታ መንግስታዊ ካልሆኑ የልማት ድርጅቶች የቀረበውን የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄ  ተከትሎ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ፕሮጀክት ግምገማ ቡድን አባላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………………………….

  • የአፍሪካ የበየነ መረብ ነፃነት ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሔደ ነው። በፎረሙ ላይም በአፍሪካ ውስጥ የበየነ መረብ (ኢንተርኔት) አገልግሎት ተጠቃሚዎች 20 በመቶ ብቻ እንደሆነና ይህንም ለማሳደግ በቁርጠኝነት መሰራት እንደሚገባ ተጠቁሟል። ኢትዮጵያ በበኩሏ የተዘጉ ድረ ገጾችን ከመክፈት አንስቶ ተደራሽነትን እስከ ማስፋት ጠንካራ ስራ እየሰራች እንደሆነም በፎረሙ ላይ ተጠቅሷል። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………………………..

  • ወደ ውጭ የሚላክ የጫት ምርት በጫነ አይሱዙ መኪና ውስጥ 7 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ 5 ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ፣ 63 ሽሕ የአሜሪካን ዶላር፣ 146 ሽሕ 500 የሳኡዲ ሪያልእንዲሁም 7ሽሕ 1 መቶ 55 ድርሃም በሕገ ወጥ መንገድ ከአገር ሊወጣ ሲል መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………………………………

  • በአፋር ክልል የአሊአዳር ወረዳ ዴሼቶ ቀበሌ 20 ክላሺንኮቭ ጠመንጃ፣ አንድ ሽጉጥ፣ 45,392 የክላሽ ጥይት፣ 8,484 የM14 ጥይትና 45 የመትረየስ ጥይት የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት እና የአፋር ክልል ሕዝብ እና የፖሊስ አባላት ባደረጉት ክትትል በቁጥጥር ሥር ውሏል። (ኤዜአ)

……………………………………………………………………………

  • -በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰውን የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭት ለመግታት መገናኛ ብዙኃንና የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማድረግ በአዳማ ስልጠና እየተሰጠ ነው።በአገሪቱ የቫይረሱ ስርጭት 4 ነጥብ 9 በመቶ ላይ መድረሱም ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያ አና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት ገልጿል። (አብመድ)

……………………………………………………………………………

  • የኢትዮ ቴሌኮምን ዋጋ ለማስላት ዓለም አቀፍ አማካሪዎች እና ባለሙያዎች እንደሚያስፈልጉት የኢትዮጵያ መንግስት አስታውቋል። የገንዘብ ሚኒስቴር የኢትዮ ቴሌኮምን ዋጋ ከማስላት ባሻገር ከስራው ምን ያህሉ ለግል ኩባንያዎች ይሸጥ የሚለውን የሚያማክረው ፍለጋ መግለጫ አውጥቷል። (ዴቼ ቬለ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here