ኢዜማ ለቀጣይ ዓመታት ፓርቲዉን የሚመሩትን እጩዎች ይፋ አደረገ

0
1120

ዕረቡ ሰኔ 1 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ( ኢዜማ ) በቀጣይ ዓመታት ፓርቲዉን ለመምራት የሚወዳደሩት እጩዎች የሚያደርጉትን የምርጫ ቅስቀሳ በማስመልከት መግለጫ ሰጥቷል።

የኢዜማ የምርጫ ኮሚቴ ጸሀፊ ቅድስት ግርማ የእጩዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ከዛሬ ሰኔ 1 ቀን 2014 ጀምሮ እሰከ ሰኔ 24 ቀን 2014 እንደሚከናወን የገለፁ ሲሆን፤ ተመራጮች የፓርቲዉን ህግ እና ደንብ ማክበር ይኖርባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል።

ማንኛዉም እጩ ተወዳዳሪ በውድድር ወቅት የሌሎችን እጩዎች ክብር መንካት እንደማይችል፣ የፓርቲዉን የሥነ ምግባር ደንቦችን ማክበር እንደሚገባ እንዲሁም ከቡድንተኝነት መጽዳት በተለይም በመገናኛ ቡዙኃን በሚሰጡ ሀሳቦች ላይ በጥንቃቄ ማቅረብ እንደሚገባም በመግለጫው ተገልጿል።

ይህ ምርጫ ትልቅ ተቋም የሚገነባበት መሆኑን በማወቅ ፍትሀዊ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የምርጫ ኮሚቴዉ ያስታወቀ ሲሆን፤ ምርጫዉን ፍትሀዊ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን መግለፁን አሚኮ ዘግቧል።

ኢዜማ በማህበራዊ ድረገጹ ላይ ላይ የእጩዎችን ዝርዝር ማስቀመጡን በመግለጫው አስታዉቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here