ኢዜማ በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ዜጎች ላይ እየደረሱ ያሉትን ጭፍጨፋዎች በፅኑ እንደሚያወግዝ አስታወቀ

0
1033

👉መንግስት ለሚረግፉ ዜጎችን ህይወት ተጠያቂ መሆኑንንም ገልጿል

ሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ዜጎች ላይ እየደረሱ ያሉትን ጭፍጨፋዎች በፅኑ እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡

ፓርቲው እንዲህ አይነት ጭፍጨፋዎች እንዳይፈጠሩ አስቀድሞ መስራት ያለበት መንግስት ለሚረግፉ ዜጎቻችን ህይወት ተጠያቂ መሆኑን ለማስታወስ እንደሚወድም ገልጿል፡፡

የመንግስት ተቀዳሚ ተግባር የዜጎችን ደኅንነት ማስጠበቅ መሆኑን የገለፀው ኢዜማ፤ በዚህ ወቅት መንግስት የዜጎችን ደኅንነት ማስጠበቅ ሥራውን በጥንቃቄ እዲሰራ ጠይቋል።

”እንዲህ ህዝብን በሚያሸብሩ እና የዜጎችን ህይወት እንደዋዛ በሚቀጥፉ ነፍሰ በሎች ላይ እርምጃ ሲወስድ፤ በማያዳግም መንገድ እንዲሆን አልያ እንደተለመደው ነካክቶ መተው በየጊዜው የወገኖቻችንን ውድ ህይወት እያስገበረን እንደሚቀጥል ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡” ሲልም ፓርቲው በህዝብ ግንኙነቱ በኩል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የሚወሰዱ እርምጃዎችም ተመልሰው ለህብረተሰቡ የደህንንነት ስጋት መሆን በማይችሉበት ደረጃ በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲፈፀሙም ጠይቋል፡፡

በወለጋ፣ በጋምቤላ እንዲሁም በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች ከፍተኛ ግፍና መከራ ለደረሰባቸው እንዲሁም ለተጨፈጨፉ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘንም ፓርቲው ገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here