የዓባይ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ በውጭ ምንዛሬ እጥረት መጓተቱ ተገለጸ

0
867

በኹለት ዓመት እንደሚጠናቀቅ እቅድ ተይዞለት ግንባታው የተጀመረው የዓባይ ሲሚንቶ ፋብሪካ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ ቅድመ ሥራውን ከመጨረስ ፈቀቅ አለማለቱ ተገለጸ።

ጥር 16 ቀን 2011 በተካሄደው የውል ስምምነት መሠረት ወደ ግንባታ የገባው ይህ ፋብሪካ በሚጠበቀው ፍጥነት ተገንብቶ ወደ ሥራ እንዳይገባ የግንባታ ግብአት እጥረት ማነቆ ሆኖበታል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ በመቶኛ ይሄን ያህል ደረጃ ደርሷል ማለት እንደማይቻል የተነገረ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱን ለመጀመር የሚያስፈልጉ የመንገድ፣ የውኃና ኃይል አቅርቦትን የመሳሰሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ግን መጠናቀቃቸው ተነግሯል።

የኮንትራትና የዲዛይን ሥራው አልቋል የተባለ ሲሆን፣ የግንባታው ሥራ ባይቆምም ፋብሪካውን ሳይት ላይ ለመትከል የሚያስችለውን ሥራ ምንዛሬ ማግኘት ባለመቻሉ ግንባታው ተጓቷል መባሉ ተሰምቷል።

አብዛኛው የግንባታ ዕቃ በባህሪው ከውጭ የሚገባ በመሆኑ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚጠይቅ ስለሆነ፣ አሁን ባለው ሁኔታ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ስላልተቻለ መጓተቱ ታውቋል።

የዓባይ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ተጠናቆ ወደማምረት ከተሸጋገረ፣ በዓመት 2 ነጥብ 25 ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ ማምረት ይችላል የተባለ ሲሆን፣ ትልቅ ፕሮጀክት በመሆኑ አሁን ያለውን የሲሚንቶ እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያቃልለውም ተጠቅሷል።


ቅጽ 4 ቁጥር 192 ሐምሌ 2 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here