የሆቴል ቱሪዝም ዘርፍን ያነቃቃል የተባለለት የሆቴል ግብአት አቅራቢዎች ኤክስፖ ሊካሄድ ነው ሲል ግራንድ ኤልያና ሆቴል አስታወቀ።
የሆቴሉ አስተዳደር ጉዳዩን በሚመለከት ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጠበት ወቅት እንደገለፀው፤ ኤክስፖው በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቀዛቀዘውን የሆቴል ቱሪዝም ዘርፍን ለማነቃቃትና በፍላጎትና አቅርቦት መካከል ያለውን ክፍተት ለመገንባት ታልሞ የተዘጋጀ ነው ብሏል።
የግራንድ ኤልያና ሆቴል በያዝነው ወር ስለሚጀምረው ኤክስፖ ይፋ ባደረገበት መግለጫው፣ ኤክስፖው ሰዎችና አቅራቢዎች አብረው የሚሰሩበትን መንገድ የሚቀይር የትብብር መድረክ እንደሚሆን በመታመኑ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡
በዚህ ኤክስፖ ከ200 በላይ ተሳታፊዎች እና 10ሺህ በላይ ጎብኚዎች ይገኛሉ ተብሎ መጠበቁን፣ እንዲሁም የኤክስፖው ቀን ሀምሌ 12 እና 13 መሆኑንም ሆቴሉ አሳውቋል።
በኮቪድ 19 ሳቢያ ተቀዛቅዞ የቆየው የቱሪዝም ሴክተር በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት ሳቢያ ይበልጡንም ተጎድቶ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም አስጎብኚዎች፣ የሆቴል ባለቤቶች እንዲሁም ከዘርፉ ጋር ግንኙነት ባላቸው ተቋማት ውስጥ ተቀጥረው በሚሰሩ ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩ ይታወቃል
ቅጽ 4 ቁጥር 192 ሐምሌ 2 2014


