የትራንስፖርት ታሪፍ ማስተካከያ ተደረገ

0
952

በነዳጅ እና የተሽከርካሪ መለዋወጫ ጭማሪ ምክንያት የትራንስፖርት ታሪፍ ማስተካከያ መደረጉን የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ከሰኔ 29/2014 ጀምሮ የተደረገውን የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ መሠረት በማድረግ፣ የአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል።

በዚህም በደረጃ አንድ በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0 ነጥብ 5360 ሲሆን፣ አዲሱ ታሪፍ 0 ነጥብ 5600 ብር በኪሎሜትር ሆኗል። ጭማሪ በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 0240 ሳንቲም ነው። ደረጃ አንድ በጠጠር መንገድ በሰው በኪሎሜትር ነባር ታሪፍ 0 ነጥብ 6150 ሲሆን፣ አዲስ ታሪፍ 0 ነጥብ 6464 ነው። ጭማሪ በሰው በኪሎሜትር 0 ነጥብ 0314 ሳንቲም ይሆናል።

ደረጃ ኹለት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0 ነጥብ 5120 ሲሆን፣ አዲስ ታሪፍ 0 ነጥብ 5420 ነው። ጭማሪ 0 ነጥብ 0300 ሳንቲም።

ደረጃ ኹለት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0.5680 ሲሆን፣ አዲስ ታሪፍ 0.6054 ብር ነው። ጭማሪ በኪሎሜትር 0.0374 ሳንቲም።

የታሪፍ ስሌቱ በ100 ኪሎ ሜትር ሲታይ ደግሞ፣ በደረጃ አንድ ተሽከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 53 ነጥብ 60 ሲሆን፣ በአዲሱ ታሪፍ ብር 56 ነጥብ 00 ሆኗል። ጭማሪ በ100 ኪሎሜትር ብር 2 ነጥብ 40 ነው።

በደረጃ ኹለት ተሽከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 51 ነጥብ 20 የሚያስከፍል ሲሆን፣ በአዲሱ ታሪፍ ብር 54 ነጥብ 20 ሆኗል። ጭማሪ በ100 ኪሎሜትር ብር 3 ነጥብ 00 ነው።

በደረጃ ሦስት ተሽከርካሪ በ100 ኪሎሜትር ለአንድ ሰው ነባር ታሪፍ በአስፋልት መንገድ ብር 47 ነጥብ 50 የሚያስከፍል ሲሆን፣ በአዲሱ ታሪፍ ብር 50 ነጥብ 81 ያስከፍላል። ጭማሪ በ100 ኪሎ ሜትር ብር 3 ነጥብ 31 ነው። ታሪፉ ማስተካከያው ከሰኔ 30 ቀን 2014 ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የጀመረ መሆኑ ተመላክቷል።


ቅጽ 4 ቁጥር 192 ሐምሌ 2 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here