ኢትዮጵያዊው የናሳ ተመራማሪ ብርሃኑ ቡልቻ (ዶክተር ኢንጂነር) ጨረቃ ላይ ውሃ ለማግኘት የሚያስችል በመጠን አነስተኛ የሆነ ቁስ የኳንተም ፊዚክስ ቀመርን በመጠቀም መሥራቱ ተገለጸ።
የተሠራው ቁስ “ሄትሮዳይን ስፔክትሮ ሜትር” የሚል ሥያሜ ያለው መሆኑን የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ናሳ መረጃ ያመላክታል።
መሣሪያው ከፍተኛ የሆነ ጨረር በመልቀቅ በጨረቃ ላይ ያሉትን የውሃ አካላት ለማጉላት እና ለመለየት ብሎም በትክክል ቦታውን ለማመላከት ያስችላልም ነው የተባለው።
እንደ ናሳ መረጃ ቀደም ሲል በተደረጉ ጥናቶች እና ሙከራዎች ጨረቃ ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ውሃ መኖሩ ቢረጋገጥም በትክክል መለየት ግን ሳይቻል ቆይቷል። ናሳ (NASA) ቀደም ብሎ ባበለፀጋቸው ቴክኖሎጂዎች ውሃን፣ ነጻ ሃይድሮጅንን እና ሃይድሮክሲልን ለየብቻ መለየት እንዳልቻለም አስታውቆ ነበር።
ቅጽ 4 ቁጥር 199 ነሐሴ 21 2014


