ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ኢንሹራንስ ለመጀመር የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ

0
976

ሰኞ መስከረም 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 በጀት አመት ለደንበኞቹ ከሚያቀርባቸው አዳዲስ ምርት እና አገልግሎቶች መካከል የሞባይል ስልክ ኢንሹራንስ አንዱ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት፤ አገልግሎቱ ደንበኞች ከኩባንያው ጋር በሚገቡት ውል መሰረት የእጅ ስልካቸው በሚጠፋበት እና በሚበላሽበት ጊዜ የሚስተናገዱበት አሰራር ነው፡፡ ኩባንያው አገልግሎቱን ለመጀመር የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ኢ-ሲም ፤ ቴሌ ድራይቭ ፤ ኮል ሲግኒቸር እና ሌሎች በርካታ ምርት እና አገልግሎቶችን ኩባንያው ለደንበኞቹ በበጀት ዓመቱ እንደሚያቀርብ ፍሬህይወት አስረድተዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 45 በመቶ የሞባይል ጣቢያዎቹ አገልግሎት ሳይሰጡ ቆይተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን አገልግሎት ያቆሙ የሞባይል ጣቢያዎቹ ወደ 15 በመቶ ዝቅ ማለቱን የገለጹት ፍሬህይወት፤ በጸጥታ መደፍረስ እና በመሰረተ ልማት ጉዳት ምክንያት ኩባንያው የሚያጣውን ገቢ ለማማካካስ አማራጭ የገቢ ምንጮችን ማሳደግ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ማስታወቃቸውን ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ዘግቧል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም አሁን የአገሪቱን የቴሌኮም ዘርፍ የተቀላቀለውን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች ወደ ፊት ዘርፉን ከሚቀላቀሉ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ጋር የሚኖረው ግንኙነት ተወዳዳሪነት ላይ የተመሰረተ እንጂ አጋርነት እንዳልሆነ ፍሬህይወት አስረድተዋል፡፡ ነገር ግን መሰረተ ልማትን በመጋራት ረገድ በጋራ የሚሰራበት አግባብ እንዳለም ጠቅሰዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here