ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የወጪ ንግድ ባለፉት ኹለት ወራት 61 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አሰታወቀ።
በ2015 በጀት ዓመት ከማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ባለፉት ኹለት ወራት ከወጪ ንግድ ገቢ 70 ነጥብ 7 አቅዶ 61 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱ ነው የተገለጸው። ይህም ከተያዘው እቅድ 87 በመቶ ማሳካት መቻሉን አመላክቷል።
የአምራች ኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ የውጪ ምንዛሬ ገቢ ኬሚካል እና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ፣ ምግብና መጠጥ፣ ጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት፣ ቆዳ እና የቆዳ ውጤቶች፣ የማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ እና ኢንጂነሪንግ ያቀዱትን ማሳካታቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አመላክቷል።
ቅጽ 4 ቁጥር 205 መስከረም 28 2015


