“ሰዋስው መልቲ ሚዲያ” የሙዚቃ መተግበሪያ አውድ ይፋ ተደረገ

0
1429

የሥራ እድል ለመፍጠር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ፣ ፈጠራ የታከለበት የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባትና ዓለም ዐቀፍ ገበያን ለመቀላቀል ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር የተነገረለት “ሰዋሰው መልቲ ሚዲያ” የሙዚቃ መተግበሪያ አውድ ይፋ ተደርጓል።

“ቱ ኤፍ ካፒታል ኃላ/የተ/ የግ ማህበር” ከራይድ ቴክኖሎጂ በመቀጠል “ሰዋሰው መልቲ ሚዲያ” የተሰኘውን ይህን የሙዚቃ መተግበሪያ አውድ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ስራ ወደ ሙዚቃ ኢንዱስትሪ ደረጃ ያሸጋግራል ተብሎለታል።

መተግበሪያውን ይፋ በማድረጊያው መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ  በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ ቴክኖሎጂው ኢትዮጵያ የያዘችውን የዲጂታላይዜሽን ጥረትን የሚደግፍ እንዲሁም ለውጭ ምንዛሬ ግኝት የራሱን አስተዋጽኦ ሊያበረክት የሚችል እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን፣ ከቴሌ ብርና ከእናት ባንክ የክፍያ ስርዓት ጋር የተሳሰረ መሆኑ ቴክኖሎጂው አንድ እርምጃ ወደፊት መጓዙን እንደሚያሳይም አመልክተዋል።

የራይድ ቴክኖሎጂ ዋና ሥራ አስፈጻሚና የሰዋስው ቦርድ ሊቀመንበር ወይዘሮ ሳምራዊት ፍቅሩ፣ ትግበራው የሙዚቃ የገበያ ዕድልን በማስፋት፣ በሥነ ጥበብ፣ በሙዚቃ ስራዎች ላይ ተሳትፎ ያለው ሁሉ እንደ አበርክቶውና ድርሻው በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚሆንበት ክፍያን እውን የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።

በመተግበሪያው ላይ አዳዲስ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ለመልቀቅ አርቲስት ግርማ ተፈራ፣ ጸጋዬ እሸቱ፣ ካሙዙ ካሳ፣ አብነት አጎናፍር፣ ሄኖክ አበበ፣ ራሄል ጌቱን ጨምሮ በርካታ አንጋፋ እና ወጣት ባለሙያዎች ስምምነት ፈጥረዋል።


ቅጽ 4 ቁጥር 206 ጥቅምት 5 2015

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here