በመንግስት ጥሪ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወደ ኢትዮጵያ ለገቡት ግለሰቦች መንግስት የሚያደርገው ጥበቃ ከፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ ጋር የሚጣረስ እንደሆነ የአዲስ በፌደራል ፖሊስ ሕግ ባለሙያ ኮማደር ፋሲል አሻግሬ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።
አክቲቪስት ጃዋር መሐመድን ጨምሮ ወደ አገር ውስጥ የገቡ ግለሰቦች ጥቃት ሊደርስባቸው ይችላል ተብሎ ጥበቃ ሲደረግላቸው የነበረ ሲሆን ይህም የፌደራል ፖሊስ ከተቋቋመበት አዋጅ ውጭ መሆኑን አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ ለግለሰቡ የሚደረገው ጥበቃ አስጊ ሁኔታ የለም ተብሎ በታሰበበት ወቅትም በማንኛውም ጊዜ ማንሳት እንደሚቻል አስታውቀዋል።
የፌደራል ፖሊስ ሲቋቋም ጥበቃ የሚደረግላቸውን ግለሰቦች የለየ ሲሆን እነዚህም መንግሥት አገርንና ሕዝብን ይጠቅማሉ ብሎ ኃላፊዎችን ሲሾም ኃላፊነቱ ቀጥታ የፖሊስ ኮሚሽን በመውሰድ ጥበቃ እንደሚያደርግ አመልክተዋል።



