በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን ፖለቲካዊ አመኔታ ወደ ተሻለ ደረጃ ማሳደግ እንደሚገባ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ተናገሩ። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ልዩ መልዕክተኛ በመሆን ከቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዋንግ ይ ጋር የተወያዩ ሙላቱ ኹለቱ አገራት የጋራ ጥቅማቸውን ከማስጠበቅ ባለፈ ያላቸውን የፖለቲካ አመኔታም ማሳደግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር በበኩላቸው ቻይናዊያን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋእለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ እንደሚያበረታቱ እና ቻይናም ቀጠናዊ እና ሉላዊ ችግሮችን ለመፍታት እንደምትተጋ አስታውቀዋል። አያይዘውም ቻይና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና በታላላቅ ግንባታዎች ለላይ ከመሳተፍ ባሻገር ታዳጊ አገራትን ጥቅመም ለማስጠበቅም እንደምትሰራ ተናግረዋል።
ሙላቱ ተሾመ በጉብኝታቸው ወቅትም የኹለቱነን አገራት አጋርነት እና ቅንጅታዊ አሰራር እንደሚጠናከር ተስፋ ስለመጣላቸው ሲጂቲኤን ዘግቧል።



