የሸገር ፕሮጀክት ምዕራፍ ኹለት በ50 ጥንዶች የሠርግ ሥነሥርዓት ሊመረቅ ነው

0
838

አዲስ አበባን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እና ለሥሟ የሚመጥን ገጽታ እንዲኖራት ታልሞ ሲሠራ የቆየው የሸገር ፕሮጀክት ምዕራፍ ኹለት በስኬት መጠናቀቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ይህ ስፍራ ለአገር ኩራት፣ ለጎብኚዎች መዳረሻ፣ ለመዲናችን ነዋሪዎች የዘወትር መገልገያ እንዲሆን መዘጋጀቱንም ነው ያመለከተው። የሸገር ፕሮጀክት ምዕራፍ ኹለት መጠናቀቁን በማስመልከትም፥ ለምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ልዩ ስጦታ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

ጽሕፈት ቤቱ ጋብቻቸውን ለመፈጸም የተዘጋጁ ወይም አቅደው ሳይሳካላቸው የቆዩ 50 ጥንዶችን በመሥፈርት መርጦ የጋብቻ ሥርዓታቸውን በጥቅምት 20 ቀን 2015 የወዳጅነት የሠርግ አጸድ እንዲፈጽሙ ማቀዱን አመልክቷል።

በመሆኑም፣ መሞሸር ያሰቡ ወይም ሊሞሸሩ አቅደው በልዩ ልዩ ምክንያት ሳይከውኑት የቀሩ በዚህ ዘመናዊ እና ያማረ ስፍራ ሠርጋቸውን ከሚፈጽሙ 50 ጥንዶች መካከል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።

በፕሮጀክቱ ምረቃ እለት ሠርጋቸው ከሚፈጸም 50 ጥንዶች አንዱ ለመሆን በ[email protected] ድረ ገጽ ላይ ለዚሁ የተቀመጠ ቅጽን ሞልተው እስከ ጥቅምት 14 ቀን 2015 ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ኢ-ሜይል በመላክ እንዲሳተፉ አሳስቧል።


ቅጽ 4 ቁጥር 207 ጥቅምት 12 2015

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here