ብሔራዊ የፊደል ቀን የሚከበርበት ቀን ተራዘመ

0
651

ጥቅምት 17 ሊከበር ቀን ተቆርጦለት የነበረው ብሔራዊ የፊደል ቀን “ዝክረ ፊደል” በሚል መርህ ኅዳር 10 ቀን እንዲከበር ለውጥ እንደተደረገ አዘጋጆች አስታወቁ።

በበጎ ፍቃደኛ ኢትዮጵያዊያን አስተባባሪነት የሚከበረው ቀንን ይበልጥ ታሪካዊና ውጤታማ ለማድረግ ተጨማሪ ጊዜያት እንዳስፈለጋቸው የተናገሩት አዘጋጆቹ፣ ከኅዳር 7-9/2015 የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እንደሚካሄድም ገልጸዋል።

የፊደላትን አስተዋጽኦ የሚያሳዩ በርካታ ዝግጅቶች እንደሚኖሩት በሚጠበቀው መርሀግብር ላይ ፊደላትን የሚያጎሉ አልባሳት ተዘጋጅተው የሚለበሱ ሲሆን፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ጨምሮ በርካታ እንግዶች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

ኅዳር 10/2015 በሚኖር መርሀግብር ፊደላት ላይ አስተዋጽኦ ላደረጉ ምሁራን እውቅና የሚሰጥ ሲሆን፣ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎችም እንደሚቀርቡ ለማወቅ ተችሏል።


ቅጽ 4 ቁጥር 207 ጥቅምት 12 2015

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here