ዳሸን ባንክ በ2014 በጀት ዓመት ከግብር በፊት 3.8 ቢሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ

0
917

ሐሙስ ጥቅምት 17 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 3.8 ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘቱንና ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር የ57 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ተገልጿል፡፡

ባንኩ ባለፈዉ የበጀት ዓመት ተደራሽነትን ለማስፋት፣ አዳዲስ ደንበኞችን ማፍራት፣ ከፍ ያለ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ እና የላቀ ትርፍ ማስመዝገብ መቻሉን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አስፋዉ ዓለሙ ጠቁመዋል፡፡

ባንኩ የበጀት ዓመቱን አፈጻጻም ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው 29ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ለባለአክሲዎኖች አቅርቧል፡፡ በበጀት ዓመቱ 16.7 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉን ይፋ ያደረገው ባንኩ፣ አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ22.4 በመቶ ዕድገት እንዳለው ገልጿል፡፡

በወለድ ነፃ አገልግሎት ዘርፍ የሚታየው እድገት ባለፈው በጀት ዓመትም መቀጠሉንና የባንኩ አጠቃላይ ከወለድ ነጻ ተቀማጭ ገንዘብ መጠን 5.9 ቢሊየን ብር መድረሱ ተነግሯል፡፡ የባንኩ አጠቃላይ ሃብትም 117.14 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ካባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ24 በመቶ እድገት ማሳየቱን ተመላክቷል፡፡

የባንኩ ባለአክሲዮኖች ድርሻም ወደ 14.4 ቢሊዮን ብር ከፍ ያለ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ42 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ ባለአክሲዮኖቹ ባለፈው ጉባኤያቸው ተጨማሪ ካፒታል ለማቅረብ መወሰናቸውን ተከትሎ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል መጠንም 6.9 ቢሊዮን ብር መድረሱም ተገልጿል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here