የእለት ዜና
መዝገብ

Author: መርሻ ጥሩነህ

በዓልን በሐዘን ጥላ ሥር

አሰለፍ አሰፋ ይባላሉ። ኑሯቸው በአማራ ክልል የደቡበ ወሎ ዞን መቀመጫ በሆነችው ደሴ ከተማ ሲሆን፣ የ63 ዓመት እናት ናቸው። ደሴ በሰሜኑ ጦርነት ሠለባ ከሆኑ ከተሞች መካከል አንዷ ሆና የጦርነት ጠባሳ አርፎባታል። በዚህም የደሴ ከተማዋ እናት የጦርነት ሠለባ ከሆኑት ሰዎች መካከል አንዷ…

የእነ ስብሐት ነጋ መፈታት እና የጦርነቱ ሌላ ገጽታ

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተቀሰቀሰው ጦርነት ኹለተኛ ዓመቱን ማስቆጠር ቢጀምር፣ አሁንም ድረስ ዕልባት አላገኘም። ትግራይ ክልል ውስጥ በተቀሰቀሰው ጦርነት ላይ እጃቸው አለበት ተብለው ከአንድ ዓመት በፊት በሕግ ቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው በሽብርተኝነት ክስ ሲታይ የነበሩት እነ ስብሐት ነጋን፣ መንግሥት ታኅሣሥ 29/2014…

ባልደራስ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የክስ መቀስቀስ ማስፈራሪያ እንደማይቀበል ገለጸ

ፓርቲው ወደ አገራዊ ፓርቲ እንደሚያድግ አስታውቋል በቅርቡ ክሳቸው ተቋርጦ ከዕሥር የተፈቱ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች የመንግሥት ዳግም ዕሥር ማስፈራሪያን እንደማይቀበሉት እና ሠላማዊ ትግል እንደሚቀጥሉ ገለጹ። መንግሥት ታኅሣሥ 29/2014 ክሳቸውን ተቋርጦ ከዕሥር በፈታቸው ዕሥረኞች ጉዳይ ላይ ጥር 1/2014 በተካሄደው የኢትዮጵያ…

የገና በዓል ገበያ እንዴት ዋለ?

በኢትዮጵያ በየዓመቱ በድምቀት ከሚከበሩ ዓመታዊ ክብረ በዓሎች መካከል በተለይ በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የገና በዓል ነው። የገና በዓል ሲታሰብ የተለያዩ የበዓል ማድመቂያ ዝግጅቶች ይከናወናሉ። የገና በዓልን ከቤተሰብ እስከ ወዳጅ ዘመድ ተሰባስቦ ማክበር የተለመደ ነው። ታዲያ ዘመድ አዝማድ…

ዳያስፖራዎች በኢንቨስትመንት እንዲሳተፉ አምስት ዘርፎች መዘጋጀታቸው ተገለጸ

የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ጥሪ የተደረገላቸው ዳያስፖራዎች በአምስት ዋና ዋና ኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሠማሩ በየዘርፉ ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ። በኢትዮጵያ አንድ ሚሊዮን ዳያስፖራዎች የገናን በዓል በኢትዮጵያ እንዲያከብሩ ጥሪ መቅረቡን ተከትሎ፣ ዳያስፖራዎች በተለያዩ ኢንቨስትመንት ዘርፎች መዋዕለ-ነዋያቸውን እንዲያፈሱ…

የጦርነቱ ተለዋዋጭ ኹነቶች እና የማኅበረሰቡ ሥጋት

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተጀመረው ጦርነት ኹለተኛ ዓመቱን ከጀመረ ኹለት ወራት ተቆጥረዋል፡፡ በዚህ በተራዘመው ጦርነት የተለያዩ ተለዋዋጭ ኹነቶ ተከስተዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የታዩ ተለዋዋጭ የጦርነቱ ኹነቶች አሁንም እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ በዚህ ጦርነት ከታዩ ተለዋዋጭ ኹነቶች መካከል ሳይጠበቅ የመከላከያ ከትግራይ ክልል መውጣት፣ የመከላከያን ከትግራይ…

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የአውቶሞቲቭ ፖሊሲ እያዘገጀ መሆኑ ተገለጸ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከአጋር ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን የአውቶሞቲቭ ፖሊሲ እያዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ። የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከአጋር ተቋማት ጋር በጋራ ያዘጋጀው የአውቶሞቲቭ ፖሊሲውን ረቂቅ በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ገልጸዋል። የፖሊሲውን መዘጋጀት የገለጹት ሚኒስተሯ፣ የፖሊሲ ረቂቁ የተዘጋጀው፣…

ማራቶን ሞተር ለመከላከያ ሰራዊት የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ማክሠኞ ታህሳስ 19/ 2014 (አዲስ ማለዳ) ማራቶን ሞተር ኢንጅነሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ። ማራቶን ሞተርስ ድጋፉን ያደረገዉ በዛሬዉ ዕለት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማዕከል ባስመረቀበት ሥነ ሥርዓት ላይ ሲሆን፤ በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ…

በአማራ ክልል የወደሙ አካባቢዎችን መልሶ መገንቢያ ዕቅድ ለማዘጋጀት ጥናት እየተደረገ ነው

ክልሉ ለጦርነቱ ያዞረውን በጄት የፌዴራል መንግሥት እንዲተካ ዕቅድ ተይዟል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ህወሓት በአማራ ክልል የወረራቸውን አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል የመልሶ ግንባታ ዕቅድ ለማዘጋጀት ሙሉ ጥናት እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ። መነሻውን ትግራይ ክልል ያደረገው የሰሜኑ ጦርነት ወደ አማራ…

የብሔራዊ ውይይት ውጥን እና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ

በኢትዮጵያ፣ በተለይ ከ2008 ወዲህ በተለያዩ አካባቢዎች ያጋጠመው የጸጥታ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ወደ ጦርነት ካመራ አንድ ዓመት አልፎታል። በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች እልባት አለማግኘታቸውን ተከትሎ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማሪያም ደሳለኝ ሥልጣናቸውን መልቀቃቸው የሚታወስ ነው። በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች…

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እና የዋጋ ግሽበት

በኢትዮጵያ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ከተያዘው ታኅሳስ 1/2014 ጀምሮ ቀድሞ ይሸጥበት በነበረው ዋጋ ላይ ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡ የተደረገው ማሻሻያ በአንድ ሊትር እስከ አምስት ብር የሚደርስ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርብበት ዋጋ ከሌሎች ጎረቤት አገሮች ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ መሆኑ መረጃዎች ያሳሉ፡፡…

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ትዕዛዝ ተሰጠ

ምዝገባው በዘርፉ ያለውን ሀብት ለማወቅ ይረዳል ተብሏል በኢትዮጵያ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅትነት ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ያላቸውን ሀብት እንዲያስመዘግቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ትዕዛዝ ሰጠ። በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዐዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሠረት የተመዘገቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቅጽ መሠረት…

ፈተና የገጠመው የኢትዮጵያ ቱሪዝም

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ለኢኮኖሚው ዘርፍ የሚያበረክተው አስዋጽዖ ኮቪድ-19 ከመከሰቱ በፊት በነበሩት ዓመታት ከጊዜ ወደ ጊዜ ዕድገት እያስመዘገበ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም ሀብት በአግባቡ ከተጠቀመች ለኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ይሁን እንጂ፣ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ዘረፍ…

ሱዳን የኢትዮጵያ የጀርባ ትኩሳት!

ኢትዮጵያ እና ሱዳን ለዘመናት የዘለቀ መልካም ግንኙነት ያላቸው ጎረቤት አገሮች ከመሆናቸው በላይ፣ በድንበር አካባቢ የሚገኙ ዜጎቻቸው በኢኮኖሚ እና በማኅበራዊ ጉዳዮች ጥብቅ ቁርኝት እንዳላቸው ታሪካቸው ያስረዳል። በኹለቱ አገራት መካከል ለዘመናት በመልካም ጉርብትና ላይ የተመሠረተው ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ችግሮች እየገጠሙት እንደሚገኝ…

የአቢሲኒያ ባንክ ሠራተኞች እሁድ ሥራ እንድንገባ መደረጋችን መብታችንን የሚጥስ ነው አሉ

አቢሲኒያ ባንክ የዕረፍት ቀን በሆነው እሁድ ሠራተኞቹ ሥራ እንዲገቡ ማድረጉን ተከትሎ የባንኩ ሠራተኞች መብታችን እየተጣሰ ነው ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ገለጹ። ባንኩ መብታችንን ጥሷል ያሉት ሠራተኞች፣ እስካሁን ከሦስት ሳምንታት በላይ የዕረፍት ቀናቸውን እሁድ በሥራ እንዲያሳልፉ መደረጋቸውን ጠቁመዋል። ባንኩ ሠራተኞቹን በዕረፍት ቀናቸው…

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከሱዳን አጎራባች አካባቢዎች ሠርጎ ገቦች ጥቃት እየፈጸሙ ነው ተባለ

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከሱዳን አጎራባች አካባቢዎች ሠርገው የሚገቡ ታጣቂ ኃይሎች በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ መሆኑ ተገለጸ። በክልሉ እና በሱዳን አጎራባች አካባቢዎች አልፎ አልፎ ሠርገው እየገቡ ጥቃት እየፈጸሙ ነው የተባሉት ታጣቂዎች፣ እስካሁን ጥቃት የፈጸሙት በአሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ እና በመተከል…

የጦርነት ፕሮፖጋንዳ እና ዲፕሎማሲ

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ከተጀመረ ባሳለፍነው ጥቅምት 24/2014 አንድ ዓመት አስቆጥሯል። ጦርነቱ መነሻውን በትግራይ ክልል ያድርግ እንጅ ከባለፈው ሐምሌ ወር መጀመሪያ ጀምሮ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ተስፋፍቷል። አንድ ዓመት የዘለቀው ጦርነት የኃይል ፍልሚያ ብቻ አለመሆኑን መንግሥትን ጨምሮ…

ባህር ዳር የተጠለሉ ተፈናቃዮች ከተማ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ መከልከላቸውን ተናገሩ

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ባለው ጦርነት ተፈናቅለው ባህር ዳር የተጠለሉ ተፈናቃዮች በከተማ አስተዳደሩ እንዳይንቀሳቀሱ መከልከላቸውን ተከትሎ ወደ መጡበት አካባቢ እየተመለሱ መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። በባህር ዳር ከተማ ተጠልለው የሚገኙት ተፈናቃዮች አቅም ያላቸው በከተማዋ በግላቸው ቤት ተከራይተው፣ አቅም የሌላቸው በከተማዋ በተዘጋጁ መጠለያዎች…

ለቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት የቀረበው ጥሪ የሚኖረው ፋይዳ

የአገር መከላከያ ሚኒስቴር የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት አባላት የአገር መከላከያን እንዲቀላቀሉ እና ኢትዮጵያ ከገጠማት ችግር ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት እንዲያግዙ ባሳለፍነው ሳምንት ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ነው። የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት አባላት፣ በመላው አገሪቱ በሚገኙ ከ290 በላይ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶቻቸው አማካይነት በቀድሞው…

በአዲስ አበባ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ታክሲዎች ተሳፋሪዎችን እጥፍ እያስከፈሉ ነው

በአዲስ አበባ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ታክሲዎች ተሳፋሪዎችን እጥፍ እያስከፈሉ ነውበአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች አስቸኳይ ጊዜ መታወጁን ሠበብ በማድረግ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ ተሳፋሪዎችን እጥፍ እያስከፈሉ ነው። አዲስ ማለዳ ጉዳዩን በተለያዩ የአዲስ አበባ ታክሲ መጫኛ እና ማውረጃ…

ዳሸን ባንክ “ዳሸን አሜሪካን ኤክስፕረስ” የተሰኘ አለም ዓቀፍ አገልግሎት ካርድ አስተዋወቀ

ዳሸን ባንክ “ዳሸን አሜሪካን ኤክስፕረስ” የተሰኘ አለም ዓቀፍ የ“ዴቢት” አገልግሎት ካርድ ሥራ ላይ ማዋሉን አስታወቀ። ዳሸን ባንክ ከአሜሪካን ኤክስፕረስ ጋር በመተባበር ዳሸን አሜሪካን ኤክስፕረስ የተሰኘ አለም ዓቀፍ የዴቢት አገልግሎት ካርድ ለደንበኞቹ ማቅረቡን ገልጿል። የአገልግሎት ካርዱ ከኢትዮጵያ ዉጭ በተለያየ የአለም ክፍል…

አቤቱታ የቀለበሳቸው የምርጫ ውጤቶች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ለማካሄድ በያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት አጠቃላይ ምርጫውን በአንድ ዙር ማካሄድ ባለመቻሉ የመጀመሪያውን ዙር ምርጫ ሰኔ 14/2014 ካካሄደ በኋላ፣ ኹለተኛውን ዙር ምርጫ ባሳለፍነው መስከረም 20/2014 አካሂዷል። ቦርዱ ምርጫውን በአንድ ዙር ማካሄድ ያልቻለው በጸጥታ ችግር፣…

ኢትዮጵያ ከገጠማት ችግር እንዴት ትውጣ?

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ከአንድ ዓመት በፊት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈጸሙ የተቀሰቀሰው ጦርነት፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ተስፋፍቶ ቀጥሏል። መነሻውን ትግራይ ክልል ያደረገው ጦርነት ከሐመሌ መጀመሪያ ጀምሮ በአማራ እና አፋር ክልል የተወሰነ ሲሆን፣…

በመተከል ዞን የሚገኘው ታጣቂ ቡድን በየደረሰበት ንጹኃንን እየገደለ ነው ተባለ

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን የተሠማራው መከላከያ ሠራዊት እና ሌሎች የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣ በዞኑ ታጥቆ በሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ኃይል ላይ ዕርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን ተከትሎ የታጣቂው አባላት በየደረሱበት ንጹኃን ሰዎችን እየገደሉ መሆኑ ተገለጸ። በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን፣ በተለይም በመተከል ዞን፣ በንጹኃን ዜጎች…

የጦርነቱ የአንድ ዓመት ጉዞ

በህወሓት እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር መካከል የተፈጠረው ልዩነት ከቃላት ጦርነት ወደ ጦር መመዛዝ ከተቀየረ በሚቀጥለው ረቡዕ አንደኛ ዓመቱን ያስቆጥራል፡፡ በኹለቱ ኃይሎች መካከል የተፈጠረው ልዩነት ወደ ጦርነት የተቀየረው ጥቅምት 24/2013 ሲሆን፣ የተራዘመ ጦርነት ሆኖ እንደቀጠለ ነው፡፡ ጦርነቱ ከተጀመረበት ከትግራይ…

ዙሩ የበዛው ስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ

ስድስተኛው የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ ገና ከውጥኑ ጀምሮ የተለያዩ እንቅፋቶች እየገጠሙት እንደ አጠቃላይ ምርጫነቱ ሳይሆን፣ በተለያየ ጊዜ በዙር የሚደረግ ምርጫ ሆኗል። ስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ በኮቪድ 19 መካሄድ ባለበት ጊዜ አለመካሄዱን ተከትሎ፣ ለአንድ ዓመት ተራዝሞ ከሰኔ 14/2013 ከመጀመሪያው ዙር ምርጫ እና መስከረም…

በኮንሶ ዞን አስተዳደራዊ የመዋቅር ጥያቄ በማቅረባቸው 80 ሺሕ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገለጸ

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በኮንሶ ዞን ከ2011 ጀምሮ አስተዳደራዊ የመዋቅር ጥያቄ በማቅረባቸው ከ80 ሺሕ በላይ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አስታወቀ። ለግጭት ምክንያት እንደሆነ የሚነገርለትን በአካባቢው ያለውን የመዋቅር ጥያቄ ለመመለስ ታስቦ በ2003 የክልሉ መንግሥት…

የኢሰመጉ የኹለተኛው ዙር ምርጫ ትዝብት

የስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ዋና አስተናባሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ ሰኔ 14/2013 ባካሂደበት ጊዜ ተቆርጠው በቀሩ ክልሎች ባለፈው መስከረም 20/2014 ኹለተኛውን ዙር ምርጫ አካሂዶ የምርጫ ውጤቱን ይፋ አድርጓል። መስከረም 20 በተከናወነው ኹለተኛው ዙር ምርጫ በሱማሌ እና በሐረሪ ክልል…

የኮቪድ 19 ክትባት በግል ተቋማት

በኢትዮጵያ አንድ በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዘ ግለሰብ ከተመዘገበበት ዕለት መጋቢት 4/2012 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 10/2014 ድረስ 360 ሺሕ 503 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፣ ስድስት ሺሕ 287 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘው ሕይወታቸውን አጥተዋል። እስከ ጥቅምት 10/2014 ድረስ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች 23 ሺሕ 393…

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ለውጭ ገበያ ከቀረበ ቆዳ 10.3 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ

በ2014 በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ለውጭ ገበያ ከቀረበ ቆዳና የቆዳ ምርቶች 10 ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ። ባለፈው መስከረም 30 በተጠናቀቀው የ2014 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት፣ የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከውጭ ገበያ…

error: Content is protected !!