42 ማርኬትስ  ግሩፕ 10 ሚሊዮን ዶላር  ድጋፍ ማግኘቱን ገለጸ

0
863

አፍሪካን ጨምሮ በተለያዩ አህጉሮች የሚንቀሳቀሰው 42 ማርኬትስ ግሩፕ ካፒታሉን ለማሳደግ የሚያግዘውን 10 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

ድጋፉን ያገኘው በግል ባለሀብት ከሚንቀሳቀሰውና በደቡብ ሰሀራ አገራት በቴክኖሎጂ ላይ ከሚሰራው ከኮንቨርጀንስ  ፓርተንርስ እና ከ14 ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ልማት ላይ ከሚሰሩ ታዋቂ የገንዘብ ተቋሞች ነው ተብሏል።

በዲጂታል የመሰረተ ልማት ሥራዎች ላይ የተመሰረተውን የገንዘብ አቅርቦት ፕሮጅክቱን በ296 ሚልዮን ዶላር ያጠናቀቀው 42 ማርኬትስ ግሩፕ፣ ለንግድ ድርጅቶች የገንዘብ ልውውጥ ላይ ከሚሰራው ፊንቴክ ቡድን ወስጥ አንዱ ነው።

የ42 ማርኬትስ ግሩፕ ሥራ አስኪያጅ አንድሪስ ብሪንክ እንደገለጹት፣ የተገኘው ገንዘብ ድጋፍ  የዲጂታል ገንዘብ መሰረተልማቱ ትክክለኛ መተማመኛ እንዲያገኝ ከማድረጉ ባሻገር በጎ የኢንቨስትመንት ተፅዕኖ እንዲኖረው ያደርገዋል ብለዋል።

ድርጅቱ የንግድ ድርጅቶች ከባንኮች ጋር እንዲተሳሰሩ፣ የቴክኖሎጂ ኦፕሬሽኖቻቸውን በማቀላጠፍ እና ሶፍትዌራቸውን ከዘመኑ ጋር እንዲያዘምኑ እየሰራ ይገኛል ተብሏል።

ግሩፕ ድርጅቱ በአሁኑ ጊዜ በመላው አፍሪካ፣ በዩናይትድ ኪንግደም፣ በአውሮፓ ህብረት፣ በአውስትራሊያ እና በህንድ  በሚገኙ የኢንቨስትመንት ባንኮችን እና ማዕከላዊ ባንኮች ላይ  እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

ድጋፍ ያደረጉት የአለም አቀፍ የልማትና ፋይናንስ ተቋማት  በአውሮፓ፣ በአሜሪካ እና አፍሪካ የሚገኙ ሲሆኑ   በኮንቨርጀንስ  ውስጥም መዋዕለ ነዋያቸውን የሚያፈሱ  ኢንቨስተሮች ናቸው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here