በአደጋው ሰባት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ሲደርስ ቁጥራቸዉ በውል ያልታወቁ በግና ፍየሎች ሞተዋል
ሰኞ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 30 ከቀኑ 8:30 በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የቀጨኔ መካነ መቃብር አጥር ግንብ ተደርምሶ በአጥሩ ሥር በግ ከሚነግዱ ነጋዴዎች መካከል የኹለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
‹‹ቀሪ አስከሬን ካለ›› በሚል በአሁኑ ሰዓት ፍለጋ እየተካሄደ እንደሚገኝ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ በተለይም ለብስራት ሬድዮ የተናገሩ ሲሆን፤ በአደጋው ሰባት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሕክምና ተቋማት መላካቸውንም አስታውቀዋል።
ቁጥራቸዉ ለጊዜዉ በውል ያልታወቁ በግና ፍየሎች ሞተዋል የተባለም ሲሆን፤ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በፍለጋ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።



