ከነገ ጀምሮ በመላ አገሪቱ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች የሲ ቢ ኢ ብር አገልግሎት ተግባራዊ ይደረጋል

0
547

ሰኞ ሚያዚያ 30 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኹሉም የአገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች የሲ ቢ ኢ ብር አገልግሎትን ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

የባንኩ የኮርፖሬት ኮሙኑኬሽን ዳይሬክተር አልሰን አሰፋ ዛሬ እንዳስታወቁት፤ ባንኩ ዘመናዊ፣ ለአጠቃቀም ቀላልና ፈጣን የሆነውን የሲ ቢ ኢ ብር አገልግሎትን ከነገ ግንቦት 1/2015 ጀምሮ በኹሉም የአገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ተግባራዊ ያደርጋል።

በሲቢኢ ብር መተግበሪያ እንዴት በቀላሉ ነዳጅ መቅዳት ይችላል?
የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን ወደ Play Store ወይም App Store በመግባት የሲቢኢ ብር መተግበሪያዎን ያዘምኑ (Update)!

1. የሲቢኢ ብር መተግበሪያውን ይክፈቱ፣

2. ‘Quick Pay’ ‘ክፍያ ለመፈፀም’ የሚለውን አማራጭ ይጫኑ፣

3. ‘Fuel Payment’ የሚለውን የአገልግሎት አማራጭ ይምረጡ፣

4. የነዳጅ ቀጂውን የተመዘገበ ስልክ ቁጥር ያስገቡ፣

5. የሚገዙትን የነዳጅ ክፍያ መጠን ያስገቡ፣

6. የነዳጅ አይነት ይምረጡ፣

7. የታርጋ ቁጥርዎን ያስገቡ፣

8. የሚስጥር ቁጥርዎን ያስገቡ፣

9. ‘PROCESS PAYMENT’ ‘ክፍያውን አከናውን’ የሚለውን ይጫኑ፣

10. ነዳጅ ቀጅው ክፍያውን አረጋግጦ ሲቀበል፣ ክፍያውን ማከናወንዎን የሚገልፅ መልእክት ይደርስዎታል፡፡

የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለመጫን ወይም ለማዘመን የሚከተሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ፡
ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here