ኒያላ ሞተርስ 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አከበረ

0
666

አርብ ግንቦት 11 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ከውጭ በማስመጣት የሚታወቀው ኒያላ ሞተርስ አክሲዮን ማኅበር 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ትላንት ምሽት በሸራተን አዲስ ሆቴል አክብሯል፡፡

ድርጅቱ ከ50 ዓመት በፊት ሲመሰረት በ50 ሺሕ ብር ካፒታል የኒሳን ሞዴል ተሸከርካሪዎችን በማስመጣት ሲሆን፤ አሁን ላይ በኢትዮጵያ የአውቶሞቢል አቅራቢ ዘርፍ በቀዳሚነት ከሚሰለፉት ድርጅቶች መካከል አንዱ መሆን መቻሉ በክብረ በዓሉ ላይ ተጠቁሟል፡፡

ኒያና ሞተርስ በ50 ዓመት ጉዞ ውስጥ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ በማቅረብ ስኬታማ መሆን መቻሉን የኒያላ ሞተርስ አክሲዮን ማኅበር ሥራ አስኪያጅ መስፍን ቦጋለ ገልጸዋል፡፡ የድርጅቱ አቅም እያደገ መምጣቱን ተከትሎ የዋና መስሪያ ማስፋፊያ ለማድረግ ገላን አካባቢ የማስፋፊያ ቦታ መረከቡን ሥራ አስኪያጁ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

የማስፋፊያ ሥራውን ለማስጀመር ዝግጅት ማድረጋቸውን የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ፤ ድርጅቱ ሥራውን አጠናቅሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡

በክብረ በዓሉ በላይ የተገኙት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ፣ ኒያላ ሞተርስ በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ የራሱን አሻራ ማሳረፉን ጠቁመዋል፡፡ ሚኒስትሩ አክለውም፤ ድርጅቱ የኤሌክትሮኒክስ ተሸከርካሪዎችን በአገር ውስጥ የማምረት ሥራ እንዲሰራ የጠየቁ ሲሆን፣ ሚኒሰቴር መሥሪያ ቤታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here