ዮናታን ተድላ የተባለ እና በአሜሪካ ኒውዮርክ ግዛት የሚኖር የ46 ዓመት ጎልማሳ ከትዳር አጋሩ ጋር በነበረው አለመግባባት የተነሳ ባለቤቱን እና ልጁን ገድሎ ራሱን አጠፋ። ጄኒፈር ሼቸልቲን ከተባለች ባለቤቱ ጋር ለዓመታት አብረው እንደኖሩ እና አባይነሽ የተባለች የዓመስት ዓመት ልጅ ማፍራታቸውንም ለማወቅ ተችሏል።
የኒውዮርክ ፖሊስ እንዳስታወቀው ግለሰቡ በአሰቃቂ ሁኔታ ባለቤቱን እና የአምስት ዓመት ልጁን ከገደለ በኋላ ራሱን መኝታ ቤት ውስጥ ራሱን በገመድ መስቀሉን ገልጿል። የባለቤቱ አባታ ለፖሊስ እንዳስታወቁት ዩናታን በተደጋጋሚ ፍቺ ጥያቄውን ወደ ሕግ ቦታ ምትወስደው ከሆነ እሷን እና ልጇን እንደሚገድል ይዝት እንደነበርም አስታውቀዋል።
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሦስት ዓመት በፊት በባለትዳሮቹ መካከል ተከስቶ በነበረው አለመግባባት ዮናታን ባለቤቱ እና ልጁ አካባቢ እንዳይደርስ በሕግ ታግዶ እንደነበር ተጠቅሷል። በኢንፎርሜሽ ቴክኖሊጂ ትምህርት ላይ እያለ እና ባለቤቱም በማኅበራዊ ጤና ዘርፍ የማስትሬት ዲግሪዋን በኪሎምቢያ ዩኒቨርስቲ በማጥናት ላይ ሳሉ ነበር ከ10 ዓመታት በፊት የተዋወቁት።



