የሰኔ 15ቱ የግድያ ወንጀል ምርመራ መጠናቀቁ የአማራ ክልል የሠላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ አስታወቀ

0
805

የሰኔ 15ቱ የግድያ ወንጀል ‹‹ታስቦበት፣ ክህደት የተፈጸመበትና ለስልጣን ጥም የታሰበ ነው›› ሲሉ የአማራ ክልል የሠላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ አገኘሁ ተሻገር የወንጀል ምርመራ መጠናቀቁን ባሳወቁበት ወቅት ተናገሩ።

በተፈፀመው ጥቃት  ሰለባ የሆኑ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች መካከል የአማራ ክልል ፕሬዘዳንት አምባቸው መኮንን( ዶ/ር)፣የክልሉ አደረጃጀት ዘርፍ አማካሪ  እዘዝ ዋሴ እና የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የነበሩት  ምግባሩ ከበደ ሲሆኑ በግድያው እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ እና ግድያውን መረተዋል የተባሉት በወቅቱ ክልሉ ሠላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ጽጌም ህይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው።

በሰኔ 15 የግድያ ወንጀል የተጠረጠሩ አካላት አብዛኞቹ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በታክቲክ፣ በቴክኒክ፣ በሰው ማስረጃና በፎረንሲክ የተሰበሰበው መረጃ በመጠናቀቁ በቅርቡ ለሕዝቡ ይፋ ይሆናል ሲሉ አገኘሁ ተሻገር አስታውቀዋል።

በወንጀሉ ተጠርጥረው ታስረው የነበሩ ዜጎች የዋስትና መብት የተከበረላቸው ሲሆን በወንጀሉ ተሳታፊ በሆኑ ተጠርጣሪዎች ላይ በቅረቡ  ክስ እንደሚጀመርም አማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት  ዘግቧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here