ረቡዕ ግንቦት 30 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) አልሸባብ በኢትዮጵያና ሶማሊያ ድንበር ላይ ሊያደርስ የነበረው ጥቃት መክሸፉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
አሸባሪው የአልሸባብ ቡድን ዛሬ ግንቦት 30/2015 በኢትዮ-ሶማሊያ ድንበር ዶሎ አካባቢ ሊፈጽም የነበረው የሽብር ተግባር መክሸፉን የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ ”ቡድኑ አጥፍቶ ጠፊ በማሰማራት በአካባቢው ጉዳት ለማድረስ ያደረገውን ሙከራ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የመከላከያ ሠራዊት በተሳካ ሁኔታ አክሽፎታል።” ብሏል፡፡
የሽብር ቡድኑ አባላትም ይዘውት ከመጡት መሳሪያ ጋር መደምሰሳቸው ተገልጿል።



