በጎንደር ዩንቨርሲቲ የእሳት አደጋ ተከሰተ

በጎንድር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ኅዳር 9/2012 ከቀኑ 7:15 አካባቢ አጼ ቴዎድሮስ ግቢ ህንጻ ቁጥር T-35 ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የእሳት አደጋ መከሰቱን ዩንቨርሲቲው አስታወቀ ።

የእሳት አደጋ እና የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች እንዲሁም ሰራተኞች እሳቱን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ እሳቱ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል። የአዲስ ማለዳ ምንጮች እንደገለጹትበእሳት አደጋው ምክንያት በሕይዎትም ሆነ በአካል ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ተገልጿ። ምንጮች አያይዘው እንደገለጹት የክልሉ ልዩ ኃይል ወደ ዩንቨርስቲው ቅጥር ጊቢው በመግባት የማረጋጋት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

የሕንጻዎቹ የመጨረሻ ፎቅ በችፑድ ከፍልፋይ ከመሰራቱ ጋር ተዳምሮ እሳቱ በአጭር ጊዜ ሰፊ ቦታ ሊያዳርስ እንደቻለ የአዲስ ማለዳ ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል። የአደጋው መንስኤ እስካሁን እየተጠጣራ እንደሆነና በቅርቡም ዩኒቨርስቲው እንደሚያሳውቅ ይፋ አድርጓል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here