የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ ድምጽ የመስጠት ሂደት በነገው ዕለት ኅዳር 10/2012 ይከናወናል

0
885

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እንዳስታወቀው የድምጽ ሰጪዎች ምዝገባ ሂደት ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የተጠናቀቀ መሆኑን ተከትሎ ድምጽ የመስጠት ሒደት በነገው ዕለት ኅዳር 10/2012 ይከናወናል። በመራጮች ምዝገባ ወቅት የዞኑና የክልሉ የጸጥታ አካላት፣ የፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት ለሂደቱ ሰላማዊነት ከፍተኛ ትብብር ያደረጉ ሲሆን በድምጽ አሰጣጡም ሒደት ላይ ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርጉም ጠይቋል።

በነገ ዕለት በሚካሔደው ሕዝበ ውሳኔ 10 ሺሕ በጎ ፍቃደኞች፣ 15 ሺሕ ሚሊሻ፣ ከ2500 -3000 ፖሊስ ፣ ከ250 -300 የሚጠጋ መከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንደሚሰማሩ ተገልጿል።

በሕዝበ ውሳኔው ድምፅ ከተሰጠም ሆነ ውጤት ከተገለጸ በኋላ የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ተከልክሏል፤ረቡዕ የጫት ገበያ በሁሉም የሲዳማ ዞን ተከልክሏል፤ ማክሰኞ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ዓርብ ጠዋት በሐዋሳ ሞተር ብስክሌቶች ታግደዋል።

ሕዝበ ውሳኔው ተአማኒነት ባለው መልኩ ያለምንም ችግር እንዲካሄድ ለማድረግ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላ ተካሂዶ ስልጠናም ተሰጥቷል። የምርጫ ታዛቢዎችም ተመልመለው ተሰማርተዋል። ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም በዘገባው አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here