ኢትዩጵያ እና የተባበሩት ዐረብ ኢመሬቶች በኹለቱ አገራት ጥቅም ላይ ያተኮረ ወታደራዊ ትብብር ለማድረግ ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱን የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ እና በተባበሩት ዐረብ ኢመሬቶች የመከላከያ ሚንስትር ዲኤታ መሐመድ ቢን አሕመድ አል ቦዋርዲ መካከል ተፈርሟል።
ኢትዮጵያ በኹለቱ አገራት ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት የጋራ ጥቅምን ለማስጠበቅ በተመለከተ ያላትን ቁርጠኝነት ለማ የገለፁ ሲሆን፤ መሐመድ ቢን አሕመድ በበኩላቸው ስምምነቱ ከዓለም አቀፍ አጋሮቿ ጋር የምታደርገው ስምምነት አካል እንደሆነም አስታውቀዋል።



