የሲዳማ ሪፈረንደም እየተካሔደ ነው

0
512

የሲዳማ ክልልነትን ጥያቄን በተመለከተ በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ሕዝባዊ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እየተካሔደ እንደሆነ አዲስ ማለዳ ምንጮች ከስፍራው አስታውቀዋል። በሲዳማ ዞን ባሉ 1692 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ እየተካሔደ የሚገኘው ድምጽ አሰጣጡ ዛሬ ኅዳር 10/2012 ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ መከናወን መጀመሩም ታውቋል።

በርካታ ቁጥር ያለው ሕዝብ በምርቻ ሒደቱ ላይ ድምጽ ለመስጠት እየተሳተፈ እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን፤ የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ ትንሽ ቀርፋፋ ከመሆን ውጪ ኹሉም ሒደት ሰላማዊ እና ኹሉን ያሳተፈ እንደሆነ ምንጮች አስታውቀዋል። በድምጽ አሰጣጡ ሒደት ላይ ሲዳማ ዞንን በደቡብ ክልል ውስጥ እንዲቆይ የሚለው የምርጫ ምልክት ጎጆ ቤት ምልክት ሲሆን፤ ሲዳማ በክልል ደረጃ ሊደራጅ ይባል የሚለው ደግሞ በሻፌታ የምግብ ዓይነት ተወክሏል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመካሔድ ላይ ያለውን ምርጫ በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት እና ከኅብረተሰቡ ጋር በመሆን ለሰላማዊነቱ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ባለፉት ቀናት በስፋት ማስታወቁ የሚታወስ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here