ቅዳሜ ነሐሴ 13 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ክልልን በአዲስ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሚል ለማደራጀት በወልቂጤ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ፤ እንዳሻው ጣሰውን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሹሟል።
በጉባኤው የቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው ሥልጣናቸውን ለእንደሻው ጣሰው አስረክበዋል።
እንዳሻው ጣሰው ከዚህ ቀደም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም በሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ተመድበው ማገልገላቸው ይታወቃል።



