ቅዳሜ ነሐሴ 13 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ኹለተኛ ቀኑን የያዘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ በዛሬው ወሎው፤ ጥላሁን ከበደን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።
ጥላሁን ከዚህ ቀደም የጋሞ ጎፋ ዞን አስተዳዳሪ የነበሩ ሲሆን፤ በነበራቸው የሥራ ኃላፊነት የሕዝብ አገልጋይ ሆነው የሰሩና ብቃት ያለው አመራር የሰጡ ጠንካራ መሪ መሆናቸውም በምክር ቤቱ ተብራርቷል።
በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ችግሮች ሳይበገሩ ኃላፊነታቸውን በብቃት ስለመወጣታቸውም ተጠቁሟል።
ጥላሁን የሕዝብን ድምጽ የሚያከብሩ፣ በብዝሀነት የሚያምኑ ኹሉንም ሕዝብ ያለ አድሎ ያገለገሉ እንደነበርም በምክር ቤቱ አባላት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
ምክር ቤቱ የርዕሰ መስተዳድሩን ሹመት በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ ፀሐይ ወረሳ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ እንዲሆኑ በሙሉ ድምፅ መርጧል።

ፀሐይ ወረሳ በጌዴኦ ዞን ከመምህርነት እስከ ዞኑ ከፍተኛ አመራነት ያገለገሉና በአሁኑ ጊዜ በፌዴሬሽን ምክር ቤት በምኒስትር ደኤታ ማዕረግ የሕገ መንግሥት ትርጉም ጻሐፊ ሆነው እያገለገሉ ያሉ ጠንካራ አመራር መሆናቸው ተገልጿል።



