ማይክ ሐመር ከትናንት ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 3 ድረስ በናይሮቢና አዲስ አበባ ጉብኝት እያደረጉ መሆኑ ተገለጸ

0
308

ማክሰኞ ነሐሴ 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ከትናንት ነሐሴ 22 ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 3/2015 ድረስ በናይሮቢና አዲስ አበባ ቆይታ እንደሚያደርጉ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።

በዚያም ከኬንያ እና ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት፣ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) እንዲሁም ከሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ይገናኛሉ ተብሏል።

ሐመር በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታም፤ በኢትዮጵያ ጦርነትን የማቆም ስምምነት አፈጻጸም ላይ እንዲሁም በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች በድርድር እንዲፈቱና ሰላማዊ ሰዎች ከጥቃት እንዲጠበቁ ግፊት ያደርጋሉ።

እንዲሁም በሱዳን ቀውስ እና ጦርነቱን ለማስቆም፣ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማስፈን፣ ፍትህ እና ተጠያቂነትን ለመደገፍ እየተደረጉ በሚገኙ ቀጠናዊና ዓለማቀፋዊ ጥረቶች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here